28
May
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በኢትዮጵያ እንደ አዲስ እየተባባሱ የመጡት የሲቪክ ምህዳሩን የሚያጣብቡ ድርጊቶች እንዳሳሰቡት አስታውቋል። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን “መልሼ አደራጃለሁ” የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ቀርቶታል። ይኼውም የጸጥታ እና ደህንነት አካላት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምርመራ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን እያዋከቡ ከመሆኑንም ባሻገር በቲያትር እና…