24
Jul
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያኹ ለመንግስታቸዉ ከኢትዮጵያዉያን ቤተ እስራኤላውያን ማህበረሰብ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ማጠናከር ባለባቸዉ ጉዳዮች ላይ ያቀረቡት እቅድ ጸድቋል። በዚህ እቅድ መሰረትም 2 ሺህ ቤተእስራኤላውያንን ወደ ቴልአቪቭ ለመዉሰድ ማቀዳቸዉን ጀረሰላም ፖስት ዘግቧል። እ.ኤ.አ በ 2015 የእስራኤል መንግስት 9 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን እስራኤል መግባት የሚፈልጉ ቤተ እስራኤላውያንን ጥያቄ ከተቀበለ በኋላ ባገጠመዉ የበጀት እጥረት ማጓጓዝ ሳይችል መቅረቱ ተዘግቧል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ የተባለዉ እቅድ ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊያንን ለማጓጓዝ 66 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተይዞለታልም ተብሏል። የሀገሪቱ መንግስት በእስራል ከሚገኙ ከ 160 ሺህ በላይ ቤተ እስራኤላውያን ዜጎች ጋር ያለዉን ግንኙነት በማጠናከር በተለይም ወደ ሀገሪቱ የጦር ሀይል ለማካተት እቅድ እንዳለዉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። በተጨማሪም በእስራኤላውያን…