11
Aug
እስራኤል ከአማራ ክልል 200 የሚሆኑ ዜጎቿንና አይሁዳውያንን ማስወጣቷን አስታወቀች። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በጋራ ባወጡት መግለጫ በክልሉ በተነሳው ግጭት 174 እስራኤላዊያንና ወደ ሀገሪቱ ለመግባት ብቁ የሆኑ ቤተ-እስራኤላዊያን ከጎንደር እንዲወጡ ተደርጓል። ሌሎች 30 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ከባህር ዳር መውጣታቸው ተነግሯል። በአራት በረራዎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የተደረጉት ዜጎች አዲስ አበባ ደርሰዋል ተብሏል። ከአዲስ አበባም ወደ እስራኤል ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢላይ ኮን እስራኤላዊያኑ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እስኪወስኑ ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚቆዩ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ መቆየትም እንደሚችሉም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እስራኤል ዜጎቿን የትም ይሁኑ የት ጥበቃ እንደምታደርግላቸው መናገራቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኸን ዘግቧል። ጠቅላይ ሚንስትሩ "አጭር፣ ኮሽታ…