01
Mar
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጉልህ ታሪክ ያለው እና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ባለሃብቶች ጥያቄያ አቅርበዋል። ከኳታር ትልልቅ ባንኮች የአንደኛው ሊቀ መንበር የሆኑት ሼክ ጃስሚ ቢን ሃማድ አል ታኒ ፋውንዴሽናቸው ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቡን አረጋግጠዋል። ቢቢሲ መረዳት እንደቻለው የሰር ጂም ራትክሊፍ ንብረት የሆነው ኢኒዎስም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል። ቢሊዮነሩ ራትክሊፍ ማንችስተር ዩናይትድን የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ቀድመው አሳውቀው ነበር። በ2005 (እአአ) ማንችስተር ዩናይትድን የገዙት የግሌዘር ቤተሰቦች “ስትራቴጅክ አማራጮችን መፈለግ” በሚል ክለቡን ለመሸጥ አስበዋል። የኳታሩ ሼክ ጃሲም ክለቡን ወደ ቀድሞ ክብሩ የመመለስ ዕቅድ አለን በማለት ቡድኑን ቢገዙ ሊያደርጉ ያሰቡትን ገልጸዋል። የእግር ኳስ ቡድኑን ማጠናከር፣ የልምምድ…