humanrights

ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ሂዩማን ራይትስ ዋች በትግራይ ክልል ተፈጸመ በሚል ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት እንደማትቀበለው አስታውቃለች። በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም አሁንም በትግራይ ምዕራባዊ አካባቢዎች የሚካሄደው የዘር ማጽዳት ወንጀል መቀጠሉንና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትም ለፈጸሙት ግፍ ተጠያቂ አልተደረጉም በማለት ሂዩማን ራይት ወች ከሰሞኑ ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ መንግስት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ መንግስት በምላሹም ሪፖርቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት ነው ሲል ተችቷል። አክሎም በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮዉን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ…
Read More
በአማራ ክልል የተጀመረው “ህግ የማስከበር ዘመቻ” ለሰብዓዊ መብት ስጋት መሆኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል የተጀመረው “ህግ የማስከበር ዘመቻ” ለሰብዓዊ መብት ስጋት መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የ9 ወር የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ ባቀረበው የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባደራጃቸው ዘጠኝ የትኩረት መስኮች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተካትተዋል፡፡  በቀረበው ሪፖርት የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራን በተመለከተ ኮሚሽኑ በዋናው መሥሪያ ቤቱና በከተማ ጽሕፈት ቤቶቹ በ1491 ሰዎች 1680 ጉዳዮች ላይ አቤቱታ የቀረቡለት ሲሆን ከነዚህም መካከል በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ 1084 አቤቱታዎችን ተቀብሎ ማስተናገዱ ተገልጿል፡፡ አቤቱታ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል አብዛኞቹ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን የተቀሩትደግሞ የኢኮኖሚያዊናየማኅበራዊ መብቶችንየተመለከቱ ናቸው።  ኮሚሽኑ በ48 ማረሚያ ቤቶች እና በ323 ፖሊስ ጣቢያዎች አካሄድኩት ባለው…
Read More
ተመድ በቶርች ጉዳይ ኢትዮጵያን ሊገመግም መሆኑን አስታወቀ

ተመድ በቶርች ጉዳይ ኢትዮጵያን ሊገመግም መሆኑን አስታወቀ

የተባበሩት መንግታት ድርጅት በፈረንጆቹ 1984 ላይ በእስረኞች የሚፈጸሙ ስቃዮችን ወይም ቶርቸርን ለመከላከል በማሰብ ስምምነት አዘጋጅቶ ነበር። ይህን ስምምነት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት የተቀበሉት ሲሆን ትግበራው ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። የዚህ ስምምነት አዘጋጅ የሆነው ተመድ ስምምነቱን የተቀበሉ ሀገራት ህጉን እንዴት እየተገበሩት እንደሆነ ሊገመግም መሆኑን ለዓልዐይን በላከው መግለጫ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ፣ ኮሎምቢያ፣ ብራዚል፣ ካዛኪስታን፣ ስሎቫኪያ እና ሉግዘምበርግ ደግሞ የሚገመገሙ ሀገራት ናቸው ተብሏል። 10 አባላት ያሉት የተመድ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ሀገራቱን በጀኔቫ እንደሚገመግሙም ተገልጿል። ይህ የባለሙያዎች ቡድንም የጸረ ቶርቸር ህግ ትግበራው ግምገማው የተገምጋሚ ሀገራት ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ይገኛሉ ተብሏል። ግምገማውም ከሚያዚያ 9 ቀን እስከ…
Read More
መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ ኢሰመኮ አሳሰበ

መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ ኢሰመኮ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ የክልል ልዩ ሀይሎችን በሚመለከት በተፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። ተቋሙ እንዳለው የልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀትን ውሳኔ ትግበራ በውይይትና የሰዎችን ሰብአዊ መብቶች አደጋ ላይ በማይጥል ሁኔታ ሊከውን ይገባል ሲል አሳስቧል ኢሰመኮ መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራልና በክልል መደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ መልሶ ለማደራጀት ያሳለፈውን ውሳኔና ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ የጸጥታ መደፍረስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን በተመለከተ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ በተለይም በቆቦ፣ በባሕር ዳር፣ በወረታ፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረ ብርሃን እና በመራዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ መንገድ መዘጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥጫዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች…
Read More
የኦሮሚያ ክልል ያለበቂ ማጣራት ህጋዊ ቤቶችን እያፈረሰ እንደሆነ ኢሰመኮ ገለጸ

የኦሮሚያ ክልል ያለበቂ ማጣራት ህጋዊ ቤቶችን እያፈረሰ እንደሆነ ኢሰመኮ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ በቅርቡ በአዲስ መልክ በተደራጀው የሸገር ከተማ አስተዳደር የቤቶች ፈረሳ እና በግዳጅ ማስነሳት እየተከናወነባቸው ባሉ አካባቢዎች ምርመራ ማካሄዱን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ምርመራ ካደረገባቸው አካባቢዎች መካከል ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ መነ አብቹ እና በዙሪያው የሚገኙ አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸው። ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች በግል እና በቡድን ለኮሚሽኑ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ ከየካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል። ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያቀረቡ ሰዎችን፣ የሚመለከታቸውን የከተማ አስተዳደር እና የጸጥታ አካላት በማነጋገር፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማስነሳት ሂደቱ የሚከናወንበትን ሁኔታ እንዲሁም ቀደም ሲል የፈረሱ ቤቶችን የመስክ ምልከታ በማድረግ መረጃ እና ማስረጃ ሰብስቤያለሁም ብሏል። ለኢሰመኮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ሰዎች ለኮሚሽኑ ሲያስረዱ በየአካባቢው ከቀድሞ/ነባር ባለ ይዞታዎች ቦታ ወይም ቤት በመግዛት ኑሮ…
Read More
ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት በአሜሪካ የወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገችየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ሁሉም ተሳታፊዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን አስታውቋል። ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰችበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል።  በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል።  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ…
Read More