ethiopianews

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የዜጎች እገታ መባባሱን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የዜጎች እገታ መባባሱን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በተራዘሙ ግጭቶች ምክንያት የሚፈጸሙ እገታዎች ተባብሰው መቀጠላቸውን  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት ሳቢያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ እገታዎች መባባሳቸውን ብሏል ኢሰመኮ፡፡ ኢሰመኮ አደረኩት ባለው ማጣራት ለዘረፋ "በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች" እገታዎች እንደሚፈጸሙ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡  አጋቾች ሰላማዊ ሰዎችን በአብዛኛው በጉዞ (ትራንስፖርት) ላይ እያሉ አንዳንዴም ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው አግተው ወዳልታወቀ ቦታ በመውሰድ ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ክፍያ እንደሚጠይቁ ፤ ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ በርካታ ታጋቾች ግድያን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ በሪፖርቱ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ መብረር አቆመ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ መብረር አቆመ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ ከነገ ነሀሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቆም አስታውቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ እና ከአስመራ ወደ አዲ አበባ የሚደረጉ በረራዎችን አቋርጫለሁ ያለው አየር መንገዱ በኤርትራ ያለው አሰራር አስቸጋሪ እና ከቁጥጥሩ ውጪ መሆኑ ለበረራው መቋረጥ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡ ጉዞ ለማድረግ ቲኬት የገዙ መንገደኞችም በመረጡት አየር መንገዶች እንዲበሩ እንደሚያደርግ እና የዋጋ ጭማሪ እንደማያደርግም አየር መንገዱ ገልጿል፡፡ ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከመስከረም 30 በኋላ ወደ አስመራ እንዳይበር መከልከሏ ይታወሳል፡፡ የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከአንድ ወር በፊት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በሚጓዙ ተጋዦች ላይ “የተደራጀ እና ስልታዊ የሻንጣ ስርቆት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ፣…
Read More
ግብጽ በድጋሚ ኢትዮጵያን በጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሰሰች

ግብጽ በድጋሚ ኢትዮጵያን በጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሰሰች

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ተቃውሞ አለኝ የምትለው ግብጽ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሳለች፡፡ ግብጽ በዛሬው ዕለት ለጸጽታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸችው ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለአምስተኛ ዓመት ውሃ ሙሌት አከናውናለች ይላል፡፡ በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስደተኞች እና ግብጻዊያን አርበኞች እንደተጻፈ የተገለጸው ይህ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የግብጻዊያንን ጥቅም በሚጻረር መልኩ የውሃ ሙሌት እያካሄደች ነው ብሏል፡፡ በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደል አቲ የተፈረመው ይህ የተመድ ደብዳቤ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን በፈረንጆቹ 2015 ላይ የተፈራረሙትን ስምምነት በመጣስ የግድቡ ውሃ ሙሌት በተናጠል ተከናውኗል፣ ይህም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የግድቡን…
Read More
ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ “የእልል ያልኩ ሐበሻ” የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ “የእልል ያልኩ ሐበሻ” የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ

ወጣቱ ድምፂዊ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ የተመረጠው በሐበሻ ቢራ ፉብሪካ  ነው። በአንድ አልበም እና በተለያዮ ነጠላ ዜማዎች  ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው  ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል። "እልል ያልኩ ሀበሻ " በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት የደመቀ ዝግጅት ተካሄዷል። በቃና ዌርሀውስ በተዘጋጀው በአይነቱ ለየት ያለ ፐሮግራም  የኢትዮያዊያን ባሀል፤ ዕሴት፤ማንነት እና ወግ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ቀርበዋል። በዚህም በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባሀላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ  ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል። የዝግጅቱ ዓላማም የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች…
Read More
ኢትዮጵያ በሶማሊያ መወረሯን እንደማትረሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ

ኢትዮጵያ በሶማሊያ መወረሯን እንደማትረሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀስላሴ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚንስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት የሶማሊያ መንግሥት ውስጥ ያሉ የተወሰኑ አካላት በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ስም ማጥፋት ስራ እየሰሩ ነው ብለዋል። ሶማሊያ እንደ ሉዓላዊ ሀገር ከየትኛውም ሀገር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረት መብቷ ቢሆንም "ይህ የሚሆነው ግን ለሌላ ሀገር ስጋት በማይሆን መልኩ ነው" ሲሉም ሚንስትሩ ተናግረዋል። "በሶማሊያ ያለውን መንግሥት ያቋቋምነው እኛ ነን" ያሉት አምባሳደር ታዬ ይህን ያደረግነው አልሻባብ ስልጣን ቢይዝ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአካባቢው ሀገራት ስጋት እንደሚሆን ስለምናምን ነውም ብለዋል። የሶማሊያ ሰላም እኛን ይመለከታል፣ ሰላም እንዲመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መስዋዕትነት ከፍሏል፣ አሁንም የሶማሊያ ሁኔታ የሚያሳስበን ድንበር ዘሎ የሚመጣ ትርምስን ስለማንፈልግ ነውም…
Read More
ኢትዮጵያ ሶማሊያ ቀጠናውን ለማተራመስ ከውጭ ሃይሎች ጋር እየተባበረች ነው ስትል ከሰሰች

ኢትዮጵያ ሶማሊያ ቀጠናውን ለማተራመስ ከውጭ ሃይሎች ጋር እየተባበረች ነው ስትል ከሰሰች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሶማሊያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ መግለጫውን ያወጣው ግብጽ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሶማሊያ የጦር መሳሪያ መላኳ ከተነገረ በኋላ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ግንኙነቷ ሲሻክር፥ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ቅራኔ ውስጥ ያለችው ግብጽ ለሶማሊያ ድጋፏን አሳይታለች። ግብጽ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሞቃዲሾ ጋር የወታደራዊ ደህንነት ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን በሶማሊያ ለሚሰማራው አዲስ የሰላም አስከባሪ ተልእኮ ወታደሮች ለመላክ ፈቃደኝነቷን መግለጿም ይታወሳል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ግብጽን በስም ባይጠቅስም በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) ሽግግር ሂደት ሳይጠናቀቅ በሞቃዲሾ አዲስ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ…
Read More
ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ እንደምትጀምር ገለጸች

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀይል የማመንጨት አቅም በዕጥፍ ጨምሯል ተብሏል ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ከእጥፍ በላይ ማሳደጓን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸዉ ከግድቡ የሚመረተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል። ከዚሕ ቀደም ሥራ የጀመሩት ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያመነጩ ቆይተዋል፡፡ ሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች ደግሞ እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል እንደሚያመነጩ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የሚያወዛግባትን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችዉ ከመጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ነበር። ይህ የአፍሪካ ትልቁ ግድብ በ2014 ዓ.ም ላይ…
Read More
የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸው ተገለጸ

የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸው ተገለጸ

የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ሶማሊያ መጓዛቸውን የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ከዘጠኝ ወር በፊት በአዲስ አበባ የወደብ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ስምምነትን ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው የተበላሸ ሲሆን ሶማሊያ ከግብጽ እና ቱርክ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በአፍሪካ ትልቁን ግድብ ግንባታ መጀመሯን ተከትሎ የውሃ ድርሻዬ ነካል በሚል ቅሬታ ያላት ግብጽ ይህንን እድል በመጠቀም ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን እያደረገች ነው፡፡ ይህን ተከትሎም ግብጽ ከሶማሊያ ጋር ባደረገቻቸው ወታደራዊ ስምምነቶች አማካኝነት በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ሞቃዲሾ ልካለች፡፡ ን የተፈራረምክንያት ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው…
Read More
መዲና ኢሳ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

መዲና ኢሳ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ፔሩ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ላይ እየተሳተፉ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ከቀናት በፊት ወደ ሊማ ልካለች፡፡ እስካሁን በሁለቱም ጾታዎች የ5 ሸህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ጾታ ሜዳሊያ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በ5000 ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አሸንፈዋል፡፡ አትሌት መዲና ኢሳ ውድድሩን በ14 ደቂቃ 39 ሰከንድ 71 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌቷ ውድድሯን ያጠናቀቀችው በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ28 ሰከንዶች በማሻሻል ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ሰባተኛ ደረጃን ይዛ…
Read More
ብሪታንያ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ግጭቶች አሳስቦኛል አለች

ብሪታንያ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ግጭቶች አሳስቦኛል አለች

የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ ልማት፣ ሴቶች እና እኩልነት ሚኒስትር አኔሌሴ ዶድስ በኢትዮጵያ ጉብኘት አድርገዋል፡፡ ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ በነበራቸው የአንድ ቀን ጉብኝታቸው ከኢትዮያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር እንደተወያዩ ተገልጿል፡፡ የዩኬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉብኝቱን አስመልክቶ በድረገጹ ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ግጭቶች እንዳሳሰቡት አስታውቋል፡፡ መግለጫው አክሎም በሁለቱ ክልሎች ያሉ ግጭቶች ንጹሃን እየጎዱ ነው ያለ ሲሆን የግጭቱ ሁሉም ተሳታፊዎች አለመግባባቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል፡፡ ዩኬም ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ደህንነት እና ኢኮኖሚ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልግ ሚኒስትሯ ከአምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር በነበራቸው ውይይት ወቅት መነሳቱም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ዩኬ የዓለም አቀፍ ልማት እኩልነት እና ሴቶች ሚኒስትርን ወደ ኢትዮያ የላከችው…
Read More