27
Feb
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ታራሚዎች በቀን ለአንድ ታራሚ የሚመደበው በጀት 35 ብር ብቻ በመሆኑ በቂ ምግብ እያገኙ እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡ የተመደበው በጀት አነስተኛ መሆኑ እና የወቅታዊ የገበያ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ለታራሚዎች የሚቀርብ ምግብ በቂ እንዳይሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፤ በቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማእከል (በተለምዶ አባ ሳሙኤል) በመባል በሚጠራው ማረሚያ ቤት የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጉብኝት ማድረጉን ተናግሯል፡፡ በዚህም ከምግብ አቅርቦት ማነስ በተጨማሪ አልፎ አልፎ አጃቢ የለም በማለት በቀጠሯቸው ፍርድ ቤት እና ሆስፒታል የማይወሰዱ ታራሚዎች እንዳሉም ባደረኩት ምልከታ ለማወቅ ችያለሁ ብሏል ኢሰመኮ፡፡ የአጃቢዎች እጥረት የሚፈጠረውም በማረሚያ ቤቱ የሰው ኃይል ቁጥር ማነስ እና የመርኃ ግብር መደራረብ…