24
Oct
በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) አፈጻጸምን ከላኪዎች ጋር መገምገማቸውን አስታውቀዋል። አፈጻጸሙ በምርት ጭማሪም ሆነ በውጭ ምንዛሪ ዕድገት ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን አመላክተዋል። ይህም ከዕቅዱ 132 በመቶ መሳካቱንና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ አለው ተብሏል። በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን በማላቅ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ከዘርፉ ተዋናዮች እና ከላኪዎች ጋር የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም አመላክተዋል። ይህ በዚህ…