01
Jan
በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እየተደጋገሙ ሲሆን እስካሁን መኖሪያ ቤቶች ላይ የተወሰኑ ጉዳቶችን ከማድረስ የዘለለ ከባድ ጉዳት አላደረሱም፡፡ አደጋው እያጋጠመ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ልዩ ስሙ ፈንታሌ አካባቢ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ በአዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ባለዉ ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ምክንያት ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየለቀቁ ሲሆን እስካሁን ከ2,500 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እስካሁን ከፍተኛው 5 በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። በአደጋው ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን፤ 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ ተናግረዋል። አስተዳዳሪው አክለውም በቀን ውስጥ እስከ…