26
Mar
ኢትዮዽያ የእንግሊዙን ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ተገልጿል። ዋና መስሪያ ቤቱን በእንግሊዝ ያደረገው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮጵያን 80ኛ መዳረሻው በማድረግ ስራ መጀመሩ ተሰምቷል። ግሪን ሞሽን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ያደረገው በመኪና ኪራይ ዘርፍ ላለፉት 10 ዓመታት ሲሰራ የቆየው ኤክሰለንት የመኪና ኪራይ ድርጅት ነው፡፡ ስራውን በአዲስ አበባ እውን ለማድረግ ሁለት ዓመት የፈጀ ድርድር ሲደረግ ቆይቷል ተብሏል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ለስብሰባ ለመሳሰሉት ጉዳዮች አዲስ አበባን የሚረግጡ ተጓዦች በቆይታቸው የመኪና ኪራይ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ገና ከመምጣታቸው አስቀድሞ የመኪና አይነቱንም ክፍያውንም መፈፀም እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህ በመሆኑም የሀገርን ገፅታ ከፍ ያደርጋል የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም ለመፍጠር እድል…