AbiyAhmed

ሰላምዊት ዳዊት የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

ሰላምዊት ዳዊት የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ሰላማዊት ዳዊትን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሀላፊ አድርገው ሾሙ። የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ሶስት ከፍተኛ አመራሮች ከሀላፊነት መነሳታቸው ተገልጿል። ፓስፖርት እና መሰል የዜግነት አገልግሎቶችን ለመስጠት የተቋቋመው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ተቋም ቅሬታዎች ሲቀርቡበት ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ላለፉት አንድ ዓመት ከመንፈቅ የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን፣ በምክትል ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ፍራኦል ጣፋ እና ታምሩ ግንበቶን ከኅላፊነት አንስተዋል። የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት እና ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ ማስታዋል ገዳ ለአልዓይን እንዳሉት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከሰኔ 12 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶናል ብለዋል። እንዲሁም…
Read More
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞችን ተከለች

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞችን ተከለች

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞችን ተከለች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "በአንድ ቀን 567 ሚሊዮን ችግኞች ተተክሏል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት 567 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። በአንድ ቀን 500ሺ ችግኝ የመትከል ዘመቻ አማካኝነት በሀገሪቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግኝ ሲተክሉ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ተለቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የችግኝ ተከላው" ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት" ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በዚህ አመት ብቻ ከካርቦን ሽያጭ 52 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የችግኝ ተከላው ስራ በዚሁ ከቀጠለ ከካርቦን ሽያጭ የምታገኘው ገቢ በእጥፍ እንደሚጨምር ገልጸዋል። ይሁንና በአንድ ጀምበር ተተከለ የተባለው የችግኝ መጠን በትክክል ስለመተከሉ በገለልታኛ አካል አልተረጋገጠም።
Read More
ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአራት ወራት ውስጥ ችግራቸውን ለመፍታት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአራት ወራት ውስጥ ችግራቸውን ለመፍታት ተስማሙ

ግብጽ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ውይይት የጎረቤት ሀገራት መሪዎችን መጋበዟ ይታወሳል። ኢትዮጵያን ጨምሮ የሱዳን ጎረቤት ሀገራት በመድረኩ ላይ ለመሳተፍ ወደ ካይሮ ያመሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከውይይቱ በተጓዳኝ ከፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር መወያየታቸው ተገልጿል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መወያየታቸው ሲገለጽ የግድቡ ውሀ አሞላል ደግሞ የመሪዎቹ ዋነኛ መወያያ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በግድቡ ውሀ አሞላል ዙሪያ ግብጽን እና ሱዳንን የመጉዳት ፍላጎት የላትም የተባለ ሲሆን በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ስለመስማማታቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳንም በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለባቸውን አለመግባባት በአራት ወራት ውስጥ በሚያደርጉት ውይይት ወደ…
Read More
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄዎች በመቀበል ላይ ናቸው። የባህርዳር ህዝብን ወክለው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጥያቄ አቅርበዋል።የአብን ተወካዩ እንዳሉት "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል" ብለዋል። "ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት አልቻለም" ያሉት የምክር ቤቱ አባሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጠይቀዋል። ሌላኛው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አዳነ ተሾመ በበኩላቸው " ዜጎችን በማገት በሚሊዮን ገንዘብ መጠየቅ የዜጎችን ሰላም ወጥቶ መግባት ጥያቄ ዉስጥ ከትቶታል። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ…
Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱአስታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 29/2015 ያካሂዳል፡፡ ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸድቃል፡፡ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም ከዜጎች ደህንነት ጋር በተያያዘ ብዙ ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሶስት ወራት…
Read More
በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚቃወም እና የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚቃወም እና የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡበትን ቀን በድጋፍ ሰልፍ ሲያከብሩ በአማራ ክልል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡባትን ቀን መከራ እና ሞት እንጂ ለውጥ አላመጣልንም ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ገልጸዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በህወሃት የበላይነት ይመራ የነበረው ኢህአዴግ ህዝባዊ ተቃውሞ መበርታቱን ተከትሎ ነበር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሀይለማርያም ደሳለኝ መጋቢት 2010 ዓ.ም ስልጣን የለቀቁት፡፡ ይህን ተከትሎም አብይ አህመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ተክተው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ሹመቱን በተቀበሉበት ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ የበርካቶችን ድጋፍ እና አድናቆት ያገኙ ቢሆንም በሁለት ዓመት ውስጥ ግን ድጋፋቸው አሽቆልቁሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም…
Read More
ኢትዮጵያ ህገ ወጥ የወርቅ እና ጫት ንግድ ፈተና እንደሆነባት ገለጸች

ኢትዮጵያ ህገ ወጥ የወርቅ እና ጫት ንግድ ፈተና እንደሆነባት ገለጸች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳው ነው ብለዋል። በዘንድሮው ዓመት የወርቅ እና የጫት ምርት በኮንትሮባንድ ንግድ አማካይነት እየወጣ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ከአሶሳ 20 ኩንታል ወርቅ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ይላክ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚህ  ዓመት ግን ሶስት ኩንታል ብቻ መላኩ ለወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት ማሳያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ከእዚህ ባለፈ የታንታለም ምርት በከፍተኛ ደረጃ ጉጂ ላይ ቢመረትም በህጋዊ መንገድ ወደ ውጪ ተልኮ የውጪ ገቢ ከሚያስገኘው ይልቅ በህገ ወጥ መንገድ ለጎረቤት ሀገራት የሚሸጠው ከፍተኛ ቁጥር እንዳለው አክለው አንስተዋል፡፡ ይህንኑ ከፍተኛ…
Read More
ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግስታቸውን የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ ከአንድ የምክር ቤት አባልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዜጎችን ደህንነት እና የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛው የመንግስት ኃላፊነት ቢሆንም ይህንን እያደረጉ እንዳልሆነ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፣ ቤታቸው ይፈርሳል፣ ንብረታቸው ይወድማል የሀገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት ሀገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ፣ እና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርከታ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈፅመዋል ሲሉም ከምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ ቀርቦባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ደጋግሞ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚገደሉ ዜጎች፣ ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ወንጀሎች ፣ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች ፣ ቤት መፍረሶች…
Read More
ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከሰሞኑ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በአዲስ አበባ የነበሩት ጌታቸው ረዳ በትግራይ አዲስ የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ በሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መመረጣቸው ተነግሯል። የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) የትግርኛው አገልግሎት ክፍል እንደዘገበው፣ ጌታቸው የማዕከላዊ ኮሚቴውን አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል። የቀድሞው የሕግ መምህር ጌታቸው ረዳ፣ በመንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሪቶሪያ የሕወሓት  ዋንኛ ተደራዳሪ የነበሩ ናቸው። የሽግግር ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰች የምትገኘው ትግራይ ክልል፣ ከጦርነቱ አስቀድሞ በዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ስትመራ ነበር። ከሰሞኑ በወጡ ዘገባዎች የፌዴራሉ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትግራይ በደብረጽዮን መሪነት እንድትቀጥል አይፈልጉም። ዋሺንግተን ፖስት ይዞት በወጣው ዘገባ ዐቢይ ለትግራዩ ጦርነት መጀመር ደብረጽዮንን ይወቅሳሉ። የሕወሓት ሰዎች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ…
Read More