02
Apr
በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡበትን ቀን በድጋፍ ሰልፍ ሲያከብሩ በአማራ ክልል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡባትን ቀን መከራ እና ሞት እንጂ ለውጥ አላመጣልንም ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ገልጸዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በህወሃት የበላይነት ይመራ የነበረው ኢህአዴግ ህዝባዊ ተቃውሞ መበርታቱን ተከትሎ ነበር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሀይለማርያም ደሳለኝ መጋቢት 2010 ዓ.ም ስልጣን የለቀቁት፡፡ ይህን ተከትሎም አብይ አህመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ተክተው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ሹመቱን በተቀበሉበት ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ የበርካቶችን ድጋፍ እና አድናቆት ያገኙ ቢሆንም በሁለት ዓመት ውስጥ ግን ድጋፋቸው አሽቆልቁሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም…