20
Sep
በአማራ ክልል ለ2016 የትምህርት ዘመን 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ገደማ ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም ተባለ በአማራ ክልል ለ2016 የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከተያዘው ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል እስከ ሰኞ መስከረም 07/2016 ድረስ የተመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብቻ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን፤ ለ2016 የትምህርት ዘመን ከነሐሴ 23/2015 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ሰኞ ድረስ የተመዘገቡት ተማሪዎች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። የተማሪዎችን የምዝገባ ጊዜ እስከ ሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ነው ያሉት ኃላፊው “በተያዘው ዓመት ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ በእቅድ ተይዞ…