11
May
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል። ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ፈቃድ ማግኘቱን አስታውቋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኤምፔሳ አማካኝነት የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድን ለሳፋሪ ኮም መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡ ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ አገር ኩባንያ እንደሚያደርገው የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን አዲስ ሀላፊነት መስጠቱ ይታወሳል። አምባሳደር ሔኖክ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳዮች…