Guzarapalace

ኢትዮጵያን የጉዛራ ቤተ መንግሥት በ35 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር ጥገና ሊደረግለት ነው

ኢትዮጵያን የጉዛራ ቤተ መንግሥት በ35 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ብር ጥገና ሊደረግለት ነው

በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኘው የጉዛራ ቤተመንግሥት ከተደቀነበት የመፍረስ አደጋ ለመታደግ፤ ከፌደራል መንግሥት በተበጀተ 35 ሚሊዮን 800 ሺሕ ብር በጀት የጥገና ሥራው በዛሬው ዕለት እንደሚጀመር ተገልጿል። የጥገና ሥራው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ ግርማቸው ሙሉጌታ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ጉዛራ ቤተመንግሥት በጣና ተፋሰስ አካባቢዎች የሚገኝ የመጀመሪያው ቤተመንግሥት እንደሆነ ይነገራል። ጉዛራ ቃሉ የግዕዝ ሲሆን፤ ትርጉሙም ምቹ ማለት ነው። በጎንደር የነገሥታት ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የጉዛራን ቤተመንግሥት የመሰረቱትም ያሳነፁትም ኢትዮጵያን ከ1556-1589 ድረስ በመሩት በአፄ ሰርፀ ድንግል መሆናቸው በፁሁፍ የሰፈሩ ማስረጃዎች ያሳያሉ። የጉዛራ ቤተመንግሥት ከእንፍራንዝ በስተደቡብ 5 ኪሎሜትር ወጣ ብሎ የተሰራ…
Read More