19
Dec
ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም እና ችግር ላይ የሚገኘውን የፋይናንስ ሁኔታዋን ለመቅረፍ ያግዛት ዘንድ ከአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። በሀገሪቱ የሚታየውን አመታዊ የበጀት ጉድለቷን ለሞሙላት ያግዛት ዘንድ በልዩ ሁኔታ ከአይኤም ኤፍ ብድር መጠየቋን ዘገባው አመላክቷል። የመንግሥት ባለስለጣናት ባለፈው ሳምንት ከአለም አቀፍ ቦንድ ገዢዎች ጋር በነበራቸው ስብሰባ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2024 መጀመሪያ ሶስት ወራት ከአይ ኤም ኤፍ ጋር የብድር ስምምነት ላይ እደርሳለን ብለው እንድደሚያምኑ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ያለት የገቢ ንግድ ማስኬጃ የውጭ ምንዛሬ መጠን ክምችት ዜሮ ነጥብ ሁለት በመቶ ብቻ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ የገጠማትን የበጀት ጉድለት ለመሙላት…