ዜና

በኢትዮጵያ ማየት አቁመው ለነበሩ 217 ሰዎች የአይን ንቅለ ተከላ ተደረገላቸው

በኢትዮጵያ ማየት አቁመው ለነበሩ 217 ሰዎች የአይን ንቅለ ተከላ ተደረገላቸው

በኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ለ217 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎ የአይን ብርሃናቸው ተመለሰ በኢትዮጰያ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ለ217 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና በማድረግ የአይን ብርሃናቸው እንደተመለሰ የኢትዮጰያ ደም እና ህብረ- ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡ የተለገሰው የአይን ብሌን ንቅለ ተከላውን ለሚያከናውኑት የተለያዩ የህክምና ተቋማት በመሰራጨት በአይን ብሌን ምክንያት ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎች ላይ ቅድመ ምርመራ በማድረግ  ልገሳው  እንደተከናወነ  ተገልጿል፡፡ በቀጣይ 445 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ ቢሆንም ከፈላጊዎች አንጻር በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል። ከሞት በኃላ ሰዎች የአይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ በአዲስ አበባ ብቻ የማሰባሰብ ስራ የሚከናወን ሲሆን…
Read More
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት “ኢትዮጵያ ለዲፕሎማሲ ዝግጁ አይደለችም” ሲሉ ከሰሱ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት “ኢትዮጵያ ለዲፕሎማሲ ዝግጁ አይደለችም” ሲሉ ከሰሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ከመነጋገር ይልቅ ወደ ሌሎች ሀገራት ሽምግልና ይልካሉ ሲሉ መክሰሳቸው ይታወሳል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የገቡበትን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በንግግር ለመፍታት ኢትዮጵያ ዝግጁ አይደለችም ሲሉ ተናገሩ። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በአገሪቱ ምክር ቤት የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ መንግሥታቸው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱን ለማርገብ ፍላጎት ቢኖረውም፤ ኢትዮጵያ ግን ለውይይት ዝግጁ አይደለችም ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥቂት ቀናት በፊት “የሶማሊያ መንግሥት እኛን ከማናገር፣ በየሰፈሩ እየዞረ እኛን መክሰስ መርጧል” ብለው ከተናገሩ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሳምንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ስምምነት ውጪ በሌሎች ጉዳዮችም እየተደራደሩ መሆኑን ገለጹ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ስምምነት ውጪ በሌሎች ጉዳዮችም እየተደራደሩ መሆኑን ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ዋነኛው ነው። በቱርክ አደራዳሪነት በአንካራ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድርድር ሁለተኛው ዙር የፊታችን ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀጥላል የተባለ ሲሆን ይህ ድርድር ምን ያህል ከውጭ ጣልቃ ገብነት የተጠበቀ ነው?  የሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን ብለዋል። "ኢትዮጵያ በታሪኳ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ስትደራደር ቆይታለች፣ አንድም ጊዜ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ጥቅሟን አሳልፋ ሰጥታ አታውቅም" ብለዋል። "በአንካራ እየተካሄደ ያለው የሁለትዮሽ ድርድርም ብሔራዊ ጥቅማችንን ባስጠበቀ መንገድ ይቀጥላል" ያሉት አምባሳደር ነብዩ በድርድሩ ላይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ…
Read More
የጸጥታ ሀይሎች የአማራ ክልል ህዝብ የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ እያደረጉ ነው -ሂዩማን ራይትስ ዋች

የጸጥታ ሀይሎች የአማራ ክልል ህዝብ የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ እያደረጉ ነው -ሂዩማን ራይትስ ዋች

የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋሮች በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳላየ መሆናቸውን እንዲያቆሙ ሂዩማን ራይትስ ዋች አሳሰበ፡፡ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ አማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ አዲስ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙ ሪፖርት ካሳለፍነው ነሀሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም ባሉት 10 ወራት ውስጥ ተፈጽመዋል ባለቸው ጉዳዮች ዙሪያ አተኩሯል፡፡ በአማራ ክልል ከጤና እና ተያያዥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ያተኮረው ይህ ሪፖርት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የጤና ተቋማትን ኢላማ አድርገዋል ብሏል፡፡ ተቋሙ 58 ተጎጂዎችን እና የአይን ምስክሮችን ቃለ መጠይቅ አድርጌ አወጣሁት ባለው ሪፖርቱ ላይ እንዳለው ወታደሮች ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲገቡ ቢሞቱ ሐኪሞቹ ተጠያቂ እንደሚሆኑ…
Read More
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ መሥራች ነቢይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ መሥራች ነቢይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ መሥራቾች አንዱ የሆነው ገጣሚ፣ ተርጓሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም  ረፋዱ ላይ ህይወቱ ማለፉን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘግቧል። ነቢይ መኮንን ከአዲስ አድማስ መሥራቾች አንዱ የሆነውና በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት “ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት” ስሙ እንደሚነሳም  በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ነቢይ መኮንን በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ዋና አዘጋጅነትን ጨምሮ በርካታ በነበረው አገልግሎት የተለያዩ ስራዎቹን ለአንባቢያን አድርሷል። ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን፤ “ስውር ስፌት” ቁጥር አንድና ሁለት፣ የግጥም መድብሎችን ጨምሮ በርካታ የግጥም ስራዎችን በተለያዩ መድረኮች በማቅረብ ይታወቃል፡፡ “የኛ ሰው በአሜሪካ” የተሰኘ የጉዞ ማስታወሻ መጽሐፉም ተጠቃሽ ስራው ነው፡፡…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ድርድር ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ድርድር ጀመሩ

ቱርክ ግንኙነታቸው የሻከረውን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ማደራደር መጀመሯ ተገልጿል። ሬውተርስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስነበበው ድርድሩ በቱርክ መዲና አንካራ በመካሄድ ለይ ይገኛል። ይሁን እንጂ አደራዳሪዋ ቱርክም ሆነች ተደራዳሪዎቹ እስካሁን ማረጋገጫ አልሰጡም። የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሙአሊም ፊቂ የመሩት ልኡክ በትናንትናው እለት ወደ ቱርክ ማቅናቱን ቢዘግቡም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ አልሰጠም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣንም በአንካራ ተጀምሯል ስለተባለው ድርድር ምንም መናገር አንፈልግም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊላንድ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ እንዳልሆነ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጥር ወር ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር በደረሰችው የወደብ ስምምነት ምክንያት የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል።…
Read More
ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ዳንኤል ኃ/ሚካኤል የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተደርገው ተሾመዋል፡፡ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር (ኢዲአር) ቺፍ ቴክኒካል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ዳንኤል ኃ/ሚካኤል ከሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾመዋል። የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ለኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት አብዲ ዘነበ ምትክ ዳንኤልን ኃ/ሚካኤልን ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሆኑ መድበዋል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተጓዦችና የጭነት አገልግሎት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ይታወሳል። ማኅበሩ በየቀኑ ከ700 እስከ 1 ሺህ ሰዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ155…
Read More
ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች አስመረቀች

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች አስመረቀች

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በትናትናው እለት አስመርቃለች። በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) በትናንትናው ዕለት ተማሪዎቹን ያስመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ መካከልም በአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎቹ ይገኙበታል። በቻይና የኢትዮጵያ ኤማባሲ ተወካዮች ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ምርቃት ላይ መሳተፋቸውንም ኤምባሲው አስታውቋል። “በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU በቻይና ውስጥ ብቸኛው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል የሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ ትናንት ከተመረቁት መካከል የመጀመሪያው ዙር የአማርኛ ተማሪዎች ይገኙበታል ብሏል ኤምባሲው ባወጣው መረጃ። ኤምባሲው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠቱን አመስግኖ፤ “ይህ የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያጠናክራል” ብሏል። የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ መማሪያ…
Read More
በአማራ ክልል ደብረሲና እና አዴት ከተሞች ከ27 በላይ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ደብረሲና እና አዴት ከተሞች ከ27 በላይ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች በቀናት ልዩነት “የመንግሥት ኃይሎች” ቤት ለቤትና መንገድ ላይ ‘ሰላማዊ ሰዎችን’ መግደላቸውን የዐይን እማኞችና ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቶቹ ሰኞ ሰኔ 17 እና ረቡዕ ሰኔ 19፤ 2016 ዓ/ም መፈጸማቸው የተነገረ ሲሆን፤ በጥቃቶቹም ከ27 በላይ ንጹሃን ሰዎች እንደተገደሉ ተገልጿል። በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና አራት የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በከተማዋ ‘አጋም በር መገንጠያ’ በተባለ ሰፈር ጥቃቱ ምሽት 11፡30 አካባቢ እንደተፈጸመ የተናገሩ አንድ ከጥቃቱ የተረፉ እማኝ፤ በጥቃቱ በአብዛኛው ማዳበሪያ ለመውሰድ…
Read More
የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ልዊስ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ገልጿል፡፡ ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ተጨዋች ሉዊስ ናኒ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ባሰራጨው ቪዲዮ አስታውቋል፡፡ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚመጣው የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ ለሚገኘው መቻል እግርኳስ ክለብ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሆን ተገልጿል። ናኒ ባስተላለፈው አጭር የቪዲዮ መልዕክትም " ሰላም ኢትዮጵያውያን ሰማንያኛ አመቱን ከሚያከብረው መቻል ግብዣ ስለቀረበልኝ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል። ለእኔ ልዩ ቦታ ያላትን ኢትዮጵያ ለመጎብኘት ጓጉቻለሁ በቅርቡ እንገናኝ" ሲል ተደምጧል። መቻል እግር ኳስ ክለብ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር የተቋቋመ ቡድን ሲሆን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተወዳደረ ይገኛል፡፡ ክለቡ…
Read More