03
Jul
ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ መሥራቾች አንዱ የሆነው ገጣሚ፣ ተርጓሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ህይወቱ ማለፉን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘግቧል። ነቢይ መኮንን ከአዲስ አድማስ መሥራቾች አንዱ የሆነውና በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት “ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት” ስሙ እንደሚነሳም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ነቢይ መኮንን በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ዋና አዘጋጅነትን ጨምሮ በርካታ በነበረው አገልግሎት የተለያዩ ስራዎቹን ለአንባቢያን አድርሷል። ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን፤ “ስውር ስፌት” ቁጥር አንድና ሁለት፣ የግጥም መድብሎችን ጨምሮ በርካታ የግጥም ስራዎችን በተለያዩ መድረኮች በማቅረብ ይታወቃል፡፡ “የኛ ሰው በአሜሪካ” የተሰኘ የጉዞ ማስታወሻ መጽሐፉም ተጠቃሽ ስራው ነው፡፡…