Eyetransplant

በኢትዮጵያ ማየት አቁመው ለነበሩ 217 ሰዎች የአይን ንቅለ ተከላ ተደረገላቸው

በኢትዮጵያ ማየት አቁመው ለነበሩ 217 ሰዎች የአይን ንቅለ ተከላ ተደረገላቸው

በኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ለ217 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎ የአይን ብርሃናቸው ተመለሰ በኢትዮጰያ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ለ217 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና በማድረግ የአይን ብርሃናቸው እንደተመለሰ የኢትዮጰያ ደም እና ህብረ- ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡ የተለገሰው የአይን ብሌን ንቅለ ተከላውን ለሚያከናውኑት የተለያዩ የህክምና ተቋማት በመሰራጨት በአይን ብሌን ምክንያት ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎች ላይ ቅድመ ምርመራ በማድረግ  ልገሳው  እንደተከናወነ  ተገልጿል፡፡ በቀጣይ 445 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ ቢሆንም ከፈላጊዎች አንጻር በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል። ከሞት በኃላ ሰዎች የአይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ በአዲስ አበባ ብቻ የማሰባሰብ ስራ የሚከናወን ሲሆን…
Read More