ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኗ ተገለጸ

የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ባደረሱት ጥቃት የኢትዮጵያ ቡና ንግድ ለሶስት ቀናት ተስተጓጉሎ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት የውጪ ንግድ አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ውስጥ 350 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡ ይሁንና አፈጻጸሙ 298 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት የምትልከው ቡና በቀይ ባህር በኩል በመሆኑ እና የሀውቲ ታጣቂዎች በሚያደርሱት ጥቃት ምክንያት መስጓጎል ገጥሞት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ እንደ ዋና…
Read More
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ተስማሙ

የሁለቱ ሀገራት ማእከላዊ ባንኮች ገንዘባቸው አሁን ባለው የመግዛት አቅም ልክ 46 ቢሊዮን ብር እና 3 ቢሊየን ድርሀም ለመቀያየር ተስማምተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት የሚያስችላቸውን የመግባብያ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ ሀገራቱ ከአሜሪካን ዶላር ባለፈ እርስ በእርስ በሚያደርጓቸው ግብይቶች ብር እና ድርሀምን ለመጠቀም ነው የተስማሙት፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ ተፈራርመዋል፡፡ ሀገራቱ በቀጣይ ዝርዝር አሰራሮች እና መመሪያዎች ላይ በጥልቀት የሚወያዩ ሲሆን ግብይቱን ለማሳለጥ ገንዘባቸው አሁን ባለው የመግዛት አቅም ልክ 46 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር እና 3 ቢሊየን የዩኤኢ ድርሀም በማከላዊ ባንኮቹ በኩል ለመቀያየር ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱ አዲስ አበባ…
Read More
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ላይ የተጣለውን እገዳ ተቃወመ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ላይ የተጣለውን እገዳ ተቃወመ

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል ባለሃብቶችንና የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ይጎዳል በማለት ተቃውሟል፡፡ ኮሚሽኑ ለትራንስፖርት ሚንስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ የሕግ ድንጋጌ ሳይኖርና ግልጽ ሕግ ሳይወጣለት ከበላይ አካል በተሰጠ ትዕዛዝ ብቻ ነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ማገድ አግባብነት የለውም በማለት ቅሬታውን እንደገለጠ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የተላለፈው ውሳኔ በግብርና፣ በግብርና ምርት ማቀነባበር፣ በአበባ እርሻ ልማት፣ በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግና ግንባታ እና ሌሎች ስራዎች በተሠማሩ ባለሃብቶች እና ኩባንያዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠሩን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ኮሚሽኑ አክሎም ለአንዳንድ ኢንቨስትመንት ስራዎች ከባሕሪያቸው አንጻር በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዲያስገቡ እንዲፈቀድላቸው ሲል እንደጠየቀም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ካሳለፍነው መጋቢት ወር ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች…
Read More
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሶስት ሀገራት የተውጣጡ የጠፈር ሳይንስ ተማሪዎች ተመረቁ

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሶስት ሀገራት የተውጣጡ የጠፈር ሳይንስ ተማሪዎች ተመረቁ

ቦይንግ እና የወደፊቶቹ የአፍሪካ ጠፈር ተመራማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ አካዳሚ ወይም ፋሲሳ ከሶስት የአፍሪካ ሀገራ የተውጣጡ 300 ታዳጊዎችን በጠፈር ሳይንስ አሰልጥነው አስመርቀዋል፡፡ ለአምስት ወራት የተካሄደው ይህ ስልጠና ከኢትዮጵያ፣ ናይጀሪያ  እና ታንዛኒያ ከሚገኙ 63 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ናቸው ተብሏል፡፡ በወደፊቶቹ የአፍሪካ ጠፈር ተመራማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ አካዳሚ (Future African Space Explorers STEM Academy፣ FASESA) እና Boeing [NYSE:BA] የተዘጋጀ አዲስ የትምህርት ንቅናቄ የሆነው የመጀመሪያው ወደ ጠፈር የሚወስዱ መንገዶች ፕሮግራም ስብስብ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተመርቀዋል፡፡ ከአምስት ወራት መማር በኋላ በመላው ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ ከሚገኙ 63 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 50% ሴት ልጆችን ጨምሮ 312 ተማሪዎች ለጠፈር…
Read More
ኢትዮጵያዊያኑ በሞሮኮ በተካሄደ የቴክኖሎጂ ውድድርን በአንደኝነት አጠናቀቁ

ኢትዮጵያዊያኑ በሞሮኮ በተካሄደ የቴክኖሎጂ ውድድርን በአንደኝነት አጠናቀቁ

የኢትዮጵያ ቡድን በሞሮኮ በተካሄደው የሁዋዌ ቴክ ፎር ጉድ ክፍለ አህጉራዊ ውድድርን በአንደኝነት አጠናቋል፡፡ የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር “Huawie Seeds for the Future 2024” የቴክኖሎጂ ስልጠና መርሃ ግብር በሞሮኮ (ኢሳዉራ) ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል። ይህ ስልጠና ከምስራቅ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ የተውጣጡ 17 አገራትን አሳትፏል። ኢትዮጵያም ከስምንት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 10 ተማሪዎችን በስልጠናው ያሳተፈች ሲሆን ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል 5 ተማሪዎችን የያዘው የኢትዮጵያ አንድ ቡድን በሁዋዌ ቴክፎርጉድ ክፍለ አህጉራዊ ውድድር አንደኛ በመሆን አሸንፏል፡፡ ተማሪዎቹ በቴክ ፎር ጉድ ክፍለ አህጉራዊ (ግሎባል) ፕሮጀክት ከመወዳደራቸው በፊት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን ወስደዋል። ተሳታፊ ተማሪዎቹ በ28 ቡድኖች ተከፋፍለው ለውድድር የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ያዘጋጁ…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም 94 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

ኢትዮ ቴሌኮም 94 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። ከተገኘው ገቢ 39.9 በመቶ የድምጽ ፣ 21.7 የኢንተርኔት ፣10.2 የዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ፣ 2.5 ከቴሌብር እና 1.5 ከኢንፍራስትራክቸር እንዲሁም 5 በመቶ የሚሆነው  ደግሞ ከዲቫይስ የተገኘ ገቢ መሆነም ተገልጿል ። በበጀት ዓመቱ የኩባንያው የደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፤ በበጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ተናግረዋል። ኩባንያው በውጭ ምንዛሬ ገቢ ከሚያገኝባቸው ምንጮች 198 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለውም በ2016 በጀት ዓመት ኢትዮ ቴሌኮም 30…
Read More
ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ የቡና ንግድ በታሪክ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቷን አስታውቃለች፡፡ ኢትዮጵያ ከቡና ወጪ ንግድ በዘንድሮው በጀት አመት ከአንድ ነጥብ 4 ቢሊዮን  ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በ2016 በጀት አመት ከቡና ሽያጭ በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ የሆነ ውጤት አስመዝግባለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት 298 ሺህ 500  ቶን ቡና ለውጪ ገበያ አቅርባ 1 ነጥብ 43 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠንም ሆነ በገቢ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ  ጨምረው ገልፀዋል። የተላከው የቡና መጠን በ20 በመቶ እንዲሁም በዋጋ ደረጃም…
Read More
ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ዳንኤል ኃ/ሚካኤል የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተደርገው ተሾመዋል፡፡ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር (ኢዲአር) ቺፍ ቴክኒካል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ዳንኤል ኃ/ሚካኤል ከሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾመዋል። የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ለኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት አብዲ ዘነበ ምትክ ዳንኤልን ኃ/ሚካኤልን ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሆኑ መድበዋል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተጓዦችና የጭነት አገልግሎት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ይታወሳል። ማኅበሩ በየቀኑ ከ700 እስከ 1 ሺህ ሰዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ155…
Read More
ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገለጸ

ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገለጸ

ዋና መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት እንዳልሰጠ አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የአገሪቱን የመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት በማድረግ የደንበኞቹን ነፃነት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ ተቋሙ እንዳለው በፍርድ ቤት አማካኝነት ካልታዘዘ በስተቀር ማንኛውንም የደንበኞቹን መረጃ ለሌላ ሶስተኛ አካል አሳልፎ እንደማይሰጥ ገልጿል፡፡ ድርጅቱ እስካሁን የደንበኞቹን መረጃ እንዲሰጥ ከመንግስት ጥያቄ እንዳልቀረበለት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አካል አሳልፎ እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳልደረሰውም በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ የድርጅቱ እህት ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ በሚል ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ህጋዊ ፍቃድ ከተቀበለ ከአንድ ዓመት በኋላ ስራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት ወደ…
Read More
በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ሀይሎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ከወሰነበት ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት አልፎታል፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ለ10 ወራት የዘለቀ የአስቸኳይ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ካሳለፍነው ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀመሮም የአዋጁ ጊዜ ቢያበቃም ክልሉ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛ እና ቀወት ወረዳዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ሬዲዮ…
Read More