22
Dec
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። ኢሰመኮ ባሰባሰበው መረጃ በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት…