መነሻ ገፅ

የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርጉ መሆኑን ገለጹ

የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርጉ መሆኑን ገለጹ

የሩሲያ  የመኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆኑ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ ከሩሲያ የላዳ እና ጋዝ ግሩፕ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመጡ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ለተወካዮቹ  በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ፣ ስለዘርፉ ማበረታቻዎች እንዲሁም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ስለሆነው የድሬዳዋ የነጻ ንግድ ቀጠና አጠቃላይ ገለጻ ተደረገላቸዋል፡፡ የመኪና አምራች ኩባንያ ኃላፊዎቹ ከድሬዳዋ በተጨማሪ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ ኩባንያዎቹ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ ገበያዎች ለጤና ተቋማት፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለግልና ለህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ…
Read More
ከ10 ሺህ በላይ የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ተዘጋጀ

ከ10 ሺህ በላይ የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ተዘጋጀ

(ኢትዮ ነጋሪ፣ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ) “ዛሬን በንቃት፣ ነገን በስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ይህ ሃገር-አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ከሚያዚያ 21 እሰከ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል ተበሏል፡፡ ፌስቲቫሉ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅተ የገንዘብ ድጋፍ በሚተገበረው ከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም በኩል የሚዘጋጅ ሲሆን አምሬፍ ሄልዝ አፍሪካ ከአጋሮቹ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ፌስቲቫሉን እንደሚመራ ተገልጿል፡፡ የከፍታ የተቀናጀ የወጣቶች ፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ፓርቲ አቶ ቻላቸው ጥሩነህ እንዳሉት ወጣቶችን በተለያዩ መስኮች ብቁ ማድረግ የዚህ ፌስቲቫል ዋና አላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ፌስቲቫሉ የወጣቶች ስኬት ዕውቅና የሚሰጥበት፣ ከተለያዩ ዘርፎች የመጡ ወጣቶች ልምድ የሚለዋወጡበት፣ እንዲሁም ለበለጠ ስኬት…
Read More
በትግራይ ክልል ሁለት የቀድሞ ጦር መሪዎች በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተሾሙ

በትግራይ ክልል ሁለት የቀድሞ ጦር መሪዎች በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተሾሙ

አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እና ጀነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሾመዋል። ይኸው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ ባደረገበት ወቅት ተገልጿል። በአዲሱ ካቢኔ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ፣ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነዋል። ሹመቱ በመቐለ ከተማ ይፋ ሲደረግ የክልሉን መንግስት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ አስረክቧል። አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከብሔራዊ…
Read More
ኢትዮጵያ በ10 ዓመት ከ44 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ከሀገር እንደሸሸባት ተገለጸ

ኢትዮጵያ በ10 ዓመት ከ44 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት ከሀገር እንደሸሸባት ተገለጸ

በ10 ዓመቱ ወደ ውጪ ሸሽቷል የተባለው ሀብት ከባለፈው 44 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ10 ዓመቱ እንደሚበልጥ የጥናት ወሬውን የማክሮ ኢኮኖሚ ተንታኝና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ለሸገር ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ ተመራማሪው በከተማው ውስጥ ከመደበኛው ሥርዓት ውጪም ከፍተኛ ዶላር እንደሚገላበጥ አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ 45 ቢሊየን ዶላር በሚዘገንን ሁኔታ ከሀገር ወጥቷል ብለዋል ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ፡፡ በቅርቡ 10 ዓመት የወጣው የውጭ ምንዛሪ ከባለፈው 44 አመት እንደሚልቅ ተሰምቷል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪው በ44 ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያ የሸሸው ሀብት 31 ቢሊየን ዶላር መሆኑን በጥናት ተረጋግጦ መታተሙን ተናግረዋል፡፡ የሀብት ማሸሻ ጥድፊያው በጣም አስደንጋጭ ነው የተባለ ሲሆን ለዚህ የዶላርና የገንዘብ ፍልሰት ወይም ካፒታል ፍላይት ዋነኛው ገፊ ምክንያት በሐገር…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የጀመረበትን 50ኛ ዓመት አከበረ። አየር መንገዱ ወደ ሻንግሀይ ከተማ የካቲት 1973 የመጀመሪያ የቻይና በረራውን በማድረግ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን ከጥቅምት 1973 ጀምሮ ደግሞ መዳረሻውን ወደ ቤጂንግ ከተማ በመቀየር አገልግሎን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በ5 የመንገደኛ እና 9 የእቃ ጭነት መደበኛ በረራዎች በአጠቃላይ 66 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ 10 የቻይና ከተሞች በማድረግ ላይ ይገናል። ቤጂንግ፣ ጓንዡ፣ ሼንጁ፣ሻንግሀይ፣ ሸንዘን ፣ ውሀን፣ቻንግሻ፣ዢያመን፣ቸንዱ እና ሆንግ ኮንግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚበርባቸው የቻይና ከተሞች ናቸው። የአፍሪካ ግዙፍ የአቪዬሽን ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት። በ1945 የተመሰረተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 70ኛ የምስረታ በዓሉን ከአንድ ዓመት በፊት…
Read More
ኢትዮጵያዊው ወጣት በሚያምነው ፈረሱ ተገደለ

ኢትዮጵያዊው ወጣት በሚያምነው ፈረሱ ተገደለ

በደቡብ ኢትዮጵያ አንድ ወጣት ለጭነትና ለመጓጓዣ በሚጠቀምበት ፈረስ ህይወቱ አልፏል። በደቡብ ክልል ጌድኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ለጭነትና ለመጓጓዣ በሚጠቀምበት የገዛ ፈረሱ የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። ወጣት ቅጤሳ አለሙ በጌድኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ ከሚኖርበት የገጠር ቀበሌ እንጨት ጭኖ ወደ ከተማ በማምጣት እንጨቱን ሸጦ ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ ነበር። ይህ የ26 ዓመት ወጣት ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ወደ ቤቱ በመመለስ ላይ እያለ ፈረሱ በሞተር ብስክሌት ድምፅ ደንብሮ ወጣቱን መሬት ላይ ጥሎታል ተብሏል። ወጣቱ ከፈረሱ አንገት ላይ የነበረ ረዥም ገመድ በወገቡ እንደመቀነት ታጥቆት ኖሮ  በርግጎ በሚሮጠዉ ፈረስ መሬት ለመሬት እየተጎተተ ከድንጋይና ከግንድ ጋር ይላተማል። በአካባቢዉ ህብረተሰብ ትጋትና ርብርብ እንደምንም ፈረሱን ማስቆም…
Read More
የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና መኮንኖች ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና መኮንኖች ኢትዮጵያን ጎበኙ

የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦር አመራር መኮንኖች በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል። ኤርትራ ወታደራዊ ልኡክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዓቅም እና እየተከናወኑ ያሉ የምርምር እና ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፤ ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ባሉ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ዙሪያ ለቡድኑ አባላት ገለጻ ማድረጋቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡ የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦሩ አመራሮች ቡድን አስተባባሪ ጀነራል አብርሃ ካሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ያደረጉት ጉብኝት ለአገራቸው ብዙ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን መናገራቸው ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቴክኖሎጂው ዘርፍም አብረው መስራት የሚያስችላቸው እድል ስለመኖሩም የተገነዘቡበት ጉብኝት መሆኑን መጠቆማቸውም ተመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመት በፊት ወደ ደም አፋሳሽ…
Read More
መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ለአማርኛ እና ኦሮሚኛ ተመልካቾች አዳዲስ ፕሮግራሞችን እንደሚያቀርብ አስታወቀ

መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ለአማርኛ እና ኦሮሚኛ ተመልካቾች አዳዲስ ፕሮግራሞችን እንደሚያቀርብ አስታወቀ

ከመልቲቾይዝ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዲኤስቲቪ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች የተለያዩ መዝናኛ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የይዘት ቀንን በአዲስ አበባ ያከበረ ሲሆን በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ብዙሃን መገኛኛ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡ ድርጅቱ በዚህ ወቅት እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ሲያቀርባቸው ከነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪ አዳዲስ ይዘቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡ በድርጅቱ በኩል ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ይቀርቡ ከነበሩት ይዘቶች በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮግራሞችን በአማርኛ እና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ይዘቶችን በቅርቡ እጀምራለሁም ብሏል፡፡ ዲኤስቲቪ አሁን ላይ በአቦል ቲቪ እና አቦል ዱካ ፕሮግራሙ አደይ፣ ደራሽ፣ አስኳላ፣ ሶረኔ፣ አጋሮቹ፣ ገብርዬ እና ሌሎችንም መዝናኛዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ የመልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ገሊላ ገብረሚካኤል በፕሮግራሙ ላይ…
Read More
በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚቃወም እና የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚቃወም እና የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡበትን ቀን በድጋፍ ሰልፍ ሲያከብሩ በአማራ ክልል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን የመጡባትን ቀን መከራ እና ሞት እንጂ ለውጥ አላመጣልንም ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ገልጸዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በፊት በህወሃት የበላይነት ይመራ የነበረው ኢህአዴግ ህዝባዊ ተቃውሞ መበርታቱን ተከትሎ ነበር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሀይለማርያም ደሳለኝ መጋቢት 2010 ዓ.ም ስልጣን የለቀቁት፡፡ ይህን ተከትሎም አብይ አህመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ተክተው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ሹመቱን በተቀበሉበት ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ የበርካቶችን ድጋፍ እና አድናቆት ያገኙ ቢሆንም በሁለት ዓመት ውስጥ ግን ድጋፋቸው አሽቆልቁሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም…
Read More
የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል የድጎማ በጀት እንደሚልክ ገለጸ

የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል የድጎማ በጀት እንደሚልክ ገለጸ

የፌደራል መንግስት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መልቀቅ እንደሚጀምር የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናግረዋል። ለክልሉ የሚለቀቀው በጀት፤ ለሌሎች ክልሎች እንደሚደረገው ሁሉ በወራት ተከፋፍሎ የሚላክ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። የፌደራል መንግስት ለትግራይ በጀት ለማስተላለፍ ከስምምነት ላይ መድረሱን በተመለከተ አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ተናግረው ነበር። ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተሾሙት አቶ ጌታቸው፤ የፌደራል መንግስት በጀት መፍቀዱን፤ ሆኖም የገንዘብ መጠኑን በተመለከተ ግን “ገና እንነጋገራለን” ማለታቸው ይታወሳል። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው በበኩላቸው፤ የትግራይ ክልል በጀት “የሚታወቅ” መሆኑን ገልጸዋል። የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እስኪቋቋም የበጀት ድጎማ ሳይለቅቅ ቢቆይም፤ በክልሉ ውስጥ…
Read More