22
Jul
የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ የዓለማችን ሀገራት ላይ አዲስ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል። አዲሱ ታሪፍ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው ጠቅላላ ምርት ላይ የ35 በመቶ ገቢ እንዲቀንስ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር የአሜሪካ አስተዳደር ፖሊሲ ከሀገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ 35 በመቶ የሚሆነውን የሚነካ ነው ብለዋል። በዚህ ምክንያትም ከአሜሪካ ባለፈ አማራጭ የውጭ ገበያዎችን በመመልከት ላይ መሆናቸውንም ሻፊ ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያን ቡና ወደ ሩቅ ምስራቅ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የማስፋት እቅድ ተይዟል ተብሏል። በተያዘው በጀት ዓመት ውስጥም 20 አዳዲስ የቡና ወጪ ንግድ መዳረሻዎችን የመክፈት እቅድ እንደተያዘም ተገልጿል። እንዲሁም ዋነኛ የኢትዮጵያ ቡና ገዢ ወደ ሆኑት ቻይና፣ ጃፓን፣…