05
Sep
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ከሶማሊያ ጋር የምትዋሰንበት ምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል ከሰሞኑ ግብፅ እና ሶማልያ በቀጠናው እያረጉት ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር ሀይል የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልጿል። በኢትዮጵያ አየር ሃይል የ3ኛው አየር ምድብ የተሰጠውን ሃገራዊ ግዳጅና ተልዕኮ ለመወጣት በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአየር ምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ ገልፀዋል፡፡ አዛዡ የ3ኛው አየር ምድብ የሃገራችንን ብሎም የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ የሚገኝ የሃገር መከታና መመኪያ የሆነ ምድብ ነው ያሉ ሲሆን "ወደፊትም ኢትዮጵያን ከውስጥም ይሁን ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለመጠበቅ በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ በተሟላ…