03
Jul
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋሮች በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳላየ መሆናቸውን እንዲያቆሙ ሂዩማን ራይትስ ዋች አሳሰበ፡፡ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዋች በኢትዮጵያ አማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ አዲስ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የተቋሙ ሪፖርት ካሳለፍነው ነሀሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም ባሉት 10 ወራት ውስጥ ተፈጽመዋል ባለቸው ጉዳዮች ዙሪያ አተኩሯል፡፡ በአማራ ክልል ከጤና እና ተያያዥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ያተኮረው ይህ ሪፖርት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የጤና ተቋማትን ኢላማ አድርገዋል ብሏል፡፡ ተቋሙ 58 ተጎጂዎችን እና የአይን ምስክሮችን ቃለ መጠይቅ አድርጌ አወጣሁት ባለው ሪፖርቱ ላይ እንዳለው ወታደሮች ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲገቡ ቢሞቱ ሐኪሞቹ ተጠያቂ እንደሚሆኑ…