#Somaliland

ኢትዮጵያ የሶማሊላድ ወታደሮችን ማሰልጠን ጀመረች

ኢትዮጵያ የሶማሊላድ ወታደሮችን ማሰልጠን ጀመረች

በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ወታደሮች ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የራስ ገዟ መንግስታዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡ የሶማሊያ ወጣቶችን የጫኑ በርካታ ታታ መኪኖች ሲያልፉ መመልከታቸውን የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ወታደሮች ወታደራዊ ሥልጠና ለመውሰድ ከትናንት ማክሰኞ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በመንግሥት የሚተዳደረው የሶማሊላንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለወታደራዊ ሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ናቸው ያላቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ የሠራዊት አባላት በተሽከርካሪዎች ጉዞ ሲጀምሩ አሳይቷል። “የሶማሊላንድ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጀር ጄኔራል ኑህ እስማኢል ለሥልጠና የሚጓዙትን ሠልጣኞች ሸኝተዋል” ብሏል መንግሥታዊው የሶማሊላንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘገባው። ወታደራዊ ሥልጠናውን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ በኩልም እንዲሁም የሠራዊት…
Read More