20
May
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አብርሀም በላይ (ዶ/ር) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ሆነው ተሸመዋል፡፡ እንዲሁም አይሻ መሀመድ በአብርሀም በላይ ምትክ የሀገር መከላከያ ሚንስትር እንዲሁም የዲያፖራ ባለስልጣን ዳይሬክተር የነበሩት መሀመድ እንድሪስ (ዶ/ር) በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ተደርገው ተሹመዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአመራር ሽግሽግ ለምን እንዳደረጉ በይፋ ያላሳወቁ ሲሆን በአማራ ክልል የሚገነቡ የመስኖ ግድቦች በወቅቱ አለመጠናቀቃቸውን እና የገንዘብ ብክነት ማጋጠሙን ጉብኝቱን ባካሄዱበት ባሳለፍነው ሳምንት መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሁለት ወር በፊት ደህንነት እና ዲፕሎማሲን ጨምሮ በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ተመሳሳይ የአመራር ሽግሽግ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ…