Business

መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ሊያዛውር መሆኑን ገለጸ

መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ሊያዛውር መሆኑን ገለጸ

መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ለማዛወር ማቀዱ ተገለጸ መንግስት የተወሰኑ ተቋማትን ወደግል የማዛወር እቅድ እንዳለው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ኃይለሚካኤል በሰጡት ማብራሪያ፤ በመንግስት የአክሲዮን ድርሻ ተይዘው ያሉ ተቋማት አሉ፡፡ እነርሱን ባለሃብቶች እንዲገቡበት ይፈለጋል ብለዋል፡፡ በመንግስትና በግል አጋርነት ያሉ እንደ ቢ.ኤም ጨርቃጨርቅ፣ አፍሪካ ጁስ፣ አብያታ ሶዳ አሽ እና አምቼ በሂደት ወደግል ባለሀብቶች ለማዛወር መታቀዱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። መንግስት ባለፉት ዓመትት 300 በላይ ድርጅቶችን ወደግል ማዛወሩን ጠቁመው፤በአሁኑ ወቅትም የመንግስትን እና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ መልኩ የነበረው አሰራር የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ…
Read More
ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ቅርሶች በእንግሊዝ ተገኙ

ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ቅርሶች በእንግሊዝ ተገኙ

ከኢትዮጵያ የተዘረፉ 538 ያህል ቅርሶች በእንግሊዝ ተገኙ ከኢትዮጵያ የተዘረፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ባሕላዊ ቅርሶች በእንግሊዝ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡ ቅርሶቹ እንግሊዝ ኢትዮጵያን በፈረንጆቹ 1868 ላይ በወረረችበት ወቅት በወታደሮች መዘረፋቸውም ተጠቁሟል፡፡ “ዘ ፕሪንስ ኤንድ ዘ ፕላንደር” ወደ አማርኛ ሲመለስ “ልዑሉ እና ዘረፋው” የተሠኘ መፅሐፍ የደረሱት እንግሊዛዊው አንድሪው ሄቨንስ 538 ያህል የኢትዮጵያ ቅርሶች እንዴት ወደ እንግሊዝ እንደተወሰዱ በመፅሐፉ በዝርዝር አመላክተዋልም ነው የተባለው፡፡ ደራሲው ቅርሶቹ በለንደን እንደሚገኙ መጠቆማቸውንም ኤቭኒንግ ስታንዳርድ የተሰኘው የሀገሪቷ የዜና ምንጭ ዘግቧል። የጠቀሷቸው ቅርሶች ከጥቃቅን እና ከተቀደሱ መፅሐፍት እና ቅርሶች ጀምሮ የከበሩ መዋቢያ የዕጅ አምባሮች ፣ የነገሥታት አልባሳት ፣ የነገሥታት የጋብቻ አልባሳት ፣ ዘውድ እና ታቦታት ይገኙበታል፡፡ የእንግሊዝ ወታደሮች ቅርሶቹን በያዟቸው ቦርሳዎች እና…
Read More
ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች። የትምህርት እድሉ ከ5 አመታት በፊት የተጀመረው የ "ቻይና ኢትዮጵያ ፍሬንድሽፕ ስኮላርሺፕ አካል" ነው።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው የትምህርት ዕድሉ የተሰጠው። በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ6 ተማሪዎች የሶስተኛ ዲግሪ፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይና ቋንቋ፣ ለ12 ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪዎች የፕሮጀክት ስኮላርሺፕ እና ለአንድ ተማሪ የጥናት ፈንድ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ የተሰጠው የትምህርት እድል 2 ነጥብ 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል። የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደው ስነስርዓት…
Read More
ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ

ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ

ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ ልትከፍል ይገባል ብለዋል። የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውሀን ቤተ ሙከራ ውስጥ ማምለጡን የሚናገሩት ትራምፕ ቫይረሱ በአሜሪካ ላይ ላደረሰው ጉዳት ቻይና ካሳ እንድትከፍል ጠይቀዋል ሲል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። አሜሪካ በተደጋጋሚ የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ቤተ ሙከራ አምልጧል በሚል ስትናገር የሚሰማ ሲሆን ቻይና ግን ይህን ክስ ውድቅ አድርጋለች። የኮረና ቫይረስ በዓለም ላይ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሲገድል አሜሪካ፣ ብራዚል እና ሕንድ ብዙ ዜጎቻቸውን በሞት ያጡ ሀገራት ናቸው።
Read More
ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በሟቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በሟቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተነገረ ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል። አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል። ኢንተርኔት ከተዘጋ ዛሬ 28ኛ ቀኑን የያዙ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም። መንግሥት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት የተሉያዩ አካላት ግፊት በማድረግ ላይ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት እና ኢሰመኮ ከሰሞኑ ኢንተርኔት እንዲለቀቅ ከጠየቁ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት እቀባ ከሚፈጽሙ ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ኔትብሎክስ ከዚህ በፊት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ቲክቶክ፣ዩቲዩብ፣ቴሌግራም…
Read More
ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገር ልትልክ ነው በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገራት በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሥራ ለመላክ በመንግሥት እቅድ መያዙ ተገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም በአማራ ክልል ኹሉም ዞኖች ሰሞኑን ወደ አረብ አገር ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ወጣት ሴቶች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ኢትዮ ነጋሪ ሰምታለች፡፡ ለአብነትም በምስራቅ ጎጃም ዞን ሦስት የስልጠና ማዕከላት የተዘጋጁ ሲሆን፣ በሞጣ፣ ደብረ ማርቆስ እና ደጀን ከተሞች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች የቤት አያያዝና ሌሎች አስፈላጊ የሥራ ስልጠናዎች እንደሚሰጡኢትዮ ነጋሪ ከዞኑ መረጃ አግኝታለች፡፡ ስልጠናው ለ20 ቀን በመንግሥት በነጻ የሚሰጥ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ከስልጠናው በኋላ ፈቃደኛ የሆኑ ሴቶች ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚያቀኑበት የዚህ…
Read More
የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በማደግ በኤሮስፔስ እና በተለያዩ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድሕረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተማር ጀመረ። የአቪዬሽን አካዳሚ የአቪዬሽን ስልጠና ፕሮግራሞችን በአብራሪነት፣ የአውሮፕላን ቴክኒሻን፣ የካቢን ሰራተኛ፣ የአየር መንገድ ሽያጭ እና አገልግሎት እና ሌሎች ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።  ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካደገ በኋላ በኤሮኖቲካል ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት ቢኤስሲ ዲግሪ፣ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ቢኤ ዲግሪ እና ኤምቢኤ በአቪዬሽን ማኔጅመንት የመሳሰሉ የዲግሪ መርሃ ግብሮችን ጀምሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት "ከቀጣይ እድገትና ኢንቨስትመንት በኋላ 65 ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ…
Read More
ኤሪክ ቴን ሃግ፡ የማንችስተር ዩናይትድ ‘ለውጥ ሐዋርያ’

ኤሪክ ቴን ሃግ፡ የማንችስተር ዩናይትድ ‘ለውጥ ሐዋርያ’

ግዙፉ የለንደኑ ዌምብሊ ስታድዬም 90 ደቂቃ ሞልቷል የሚል ምልክት ሲያሳይ የዩናይትድ ደጋፊዎች በኩራት ስካርፋቸውን ወደሰማይ ሰቅለው አውለበለቡ። ቀያዮቹ ሰይጣኖችና ደጋፊዎቻቸው ይህን ስሜት ካጣጣሙ ዓመታት ተቆጥረዋል። ደጋፊዎች ፊሽካው ከመነፋቱ በፊት ድላቸውን ሲያጣጥሙ፤ ይህን ለውጥ የሾፈረው ግለሰብ የአሠልጣኞች መቆሚያ ሥፍራ ላይ ሆኖ ሁኔታውን በጥሞና ይከታተላል። ዩናይትድ ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫ ያነሳው በ2017 የአውሮፓ ሊግ ፍፃሜ ነው። ዩናይትዶች ዋንጫውን እንዳነሱ አውቀውታል። የመጨረሻዎች ሽራፊ ደቂቃዎች ያስጨነቋቸው አይመስሉም። በመጀመሪያው አጋማሽ በስድስት ደቂቃዎች ልዩነት አከታትለው ያስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎችን አስጠብቀው መውጣት ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው። ምንም እንኳ በሁለተኛው አጋማሽ ኒውካስል ዩናይትድ ተነቃቅቶ ቢመጣም ኳስና መረብን ሊያገናኝ አልቻለም። ኤሪክ ቴን ሃግ በዩናይትድ መንደር ለውጥ እያመጣ ነው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል።…
Read More
ከ18 ወራት በኋላ በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ 40 አገራት ያህል አድማ ሊመቱ ይችላሉ ተባለ

ከ18 ወራት በኋላ በሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ 40 አገራት ያህል አድማ ሊመቱ ይችላሉ ተባለ

ከዓመት ከስድስት ወር በኋላ የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሊምፒክ እስከ 40 አገራት ያክል አድማ ሊመቱ እንደሚችሉ ፖላንድ አስጠነቀቀች። የፖላንድ የስፖርት እና ቱሪዝም ሚኒስትር ካሚል ቦርትኒዙክ የፓሪስ ኦሊምፒክ ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ይህ የሚስትሩ አስተያየት የተሰማው ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በፓሪሱ 2024 ኦሊምፒክ የሩሲያ እና ቤላሩስ ዜጋ አትሌቶች እንዲሳተፉ ለመፍቀድ ማቀዱን ፖላንድ፣ ሊቱኒያ፣ ኢስቶኒያ እና ላትቪያ በጋራ መቃወማቸውን ተከትሎ ነው። ዩክሬን የሁለቱ አገራት አትሌቶች የሚሳተፉ ከሆነ በውድድሩ አልገኝም ብላለች። የኦሊምፒክ ኮሚቴው ግን በውድድሩ ላይ አድማ ማድረግ ትርፉ “አትሌቶችን መቅጣት ብቻ ነው” ብሏል። የፖላንድ የስፖርት እና የቱሪዝም ሚንስትሩ የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሳምንት በኋላ ከሚያደርገው ስብሰባ በፊት ግሬት ብሪቴን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳን…
Read More
የኳታሩ ሼክ ጃሲም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

የኳታሩ ሼክ ጃሲም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጉልህ ታሪክ ያለው እና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ባለሃብቶች ጥያቄያ አቅርበዋል። ከኳታር ትልልቅ ባንኮች የአንደኛው ሊቀ መንበር የሆኑት ሼክ ጃስሚ ቢን ሃማድ አል ታኒ ፋውንዴሽናቸው ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቡን አረጋግጠዋል። ቢቢሲ መረዳት እንደቻለው የሰር ጂም ራትክሊፍ ንብረት የሆነው ኢኒዎስም ማንችስተር ዩናይትድን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው አሳውቋል። ቢሊዮነሩ ራትክሊፍ ማንችስተር ዩናይትድን የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ቀድመው አሳውቀው ነበር። በ2005 (እአአ) ማንችስተር ዩናይትድን የገዙት የግሌዘር ቤተሰቦች “ስትራቴጅክ አማራጮችን መፈለግ” በሚል ክለቡን ለመሸጥ አስበዋል። የኳታሩ ሼክ ጃሲም ክለቡን ወደ ቀድሞ ክብሩ የመመለስ ዕቅድ አለን በማለት ቡድኑን ቢገዙ ሊያደርጉ ያሰቡትን ገልጸዋል። የእግር ኳስ ቡድኑን ማጠናከር፣ የልምምድ…
Read More