01
Mar
ለዓመታት በአፍሪካ ስፖርት ላይ ጥቁር ጥላውን እንዳጠላ ነው። በቅርቡ በተካሄደው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ የችግሩ ስፋት ታይቷል። የስፖርተኞች የዕድሜ ጉዳይ። ካሜሩን ባዘጋጀችው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ ከነበሩት አገራት መካከል አንዷ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነበረች። ነገር ግን ከጨዋታው ጅማሬ በፊት ከውድድሩ እንድትሰረዝ ተደርጓል። ምክንያቱ ደግሞ ለውድድሩ ከተላኩት ተጫዋቾች መካከል 25ቱ ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸውን የኤምአርአይ ምርመራ በማሳየቱ ነው። ከኮንጎ በተጨማሪ ቻድ እንዲሁ ተጫዋቾቿን ካሜሩን ከላከች በኋላ ከውድድሩ ተሰርዛለች። የካሜሮን እግር ኳስ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ኤቶ የኤምአርአይ ምርመራ እንዲደረግ ካዘዘ በኋላ፣ ቻድ ለውድድሩ ካቀረበቻቸው ተጫዋቾች መካከል 30ዎቹ የዕድሜ ገደቡን አልፈዋል። በመላው ዓለም የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖችን የሚያማክሩት…