ኢኮኖሚ

የመንግሥት አጠቃላይ የአገር ውስጥ የብድር እዳ ክምችት 2.5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

የመንግሥት አጠቃላይ የአገር ውስጥ የብድር እዳ ክምችት 2.5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

የመንግሥት አጠቃላይ የአገር ውስጥ የብድር ክምችት 2.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱን፣ ከዚህም ውስጥ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ ከፍተኛ ድርሻ ይይዛል ተብሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር በዕዳ አስተዳደር ክፍል በኩል ያዘጋጀውን ወርኃዊ የዕዳ ማስታወቂያ የነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም. ሪፖርት፣ የመንግሥት አገራዊ ብድር ዝርዝር መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መንግሥት እ.ኤ.አ. ከጁን 30 ቀን 2025 ጀምሮ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ብድር 2.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱን እንዳስታወቀ የሪፖርተር ዘገባ ያሳያል፡፡ ከአገር ውስጥ ብድር ድርሻ 80 በመቶ የሚይዘው በረዥም ጊዜ የሚከፈል የግምጃ ቤት ሰነድ እ.ኤ.አ. በኦገስት 2025 የግምጃ ቤት ሰነድ ግዥ ከፍተኛ እንደነበርና ከአጠቃላይ ክምችት አንፃርም 39 በመቶ እንደሚሸፍን ገልጿል፡፡ እስከ ኦገስት 2025 ድረስ ባለው የመንግሥት አጠቃላይ የአገር ውስጥ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳድግ ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳድግ ገለጸ

አየር መንገዱ ከ10 ዓመት በኋላ ዓመታዊ ገቢውን 25 ቢሊዮን ዶላር የማድረስ እቅድ እንዳለው አስታውቋል። ከ10 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡ አቶ መስፍን እንደገለጹት አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2035 ላይ 209 ዓለም አቀፍ እና 31 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች፣ 271 አውሮፕላኖች እንደሚኖሩትም ጠቅሰዋል፡፡ አየር መንገዱ 67 ነጥበ 2 ሚሊዮን መንገደኞችንም በማጓጓዝ ከ10 ዓመት በኋላ ገቢውንም 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም አዳዲስ መዳረሻዎችን በማስፋት ትስስሩን ይበልጥ ማጠናከር እና አዳዲስ መዳረሻዎችን መክፈት የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም አሁን በረራ ከሚደረግባቸው አምስቱ ክፍለ አኅጉሮች ተጨማሪ አውስትራሊያንም የሚጨመር መሆኑን…
Read More
ጣልያን በኢትዮጵያ የባቡር መስመር ግንባታ ለማድረግ ተስማማች

ጣልያን በኢትዮጵያ የባቡር መስመር ግንባታ ለማድረግ ተስማማች

የጣልያን ባቡር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ቁርጠኝነት አለኝ ብሏል። የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ  የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ የመንግስት ቁርጠኝነት ምኖሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ የህግ አገልግሎት ሃላፊ አቶ ካሳሁን ሙላቱ እንደገልፁት ኮርፖሬሽኑ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማጠናከር ከኮይፓ ኢጣሊያ ጋር ስምምነት አድርጓል። ስምምነቱ አዳዲስ የባቡር መስመሮችን መዘርጋትን እንዲሁም እየተገነቡ ያሉ የባቡር መስመሮችን በፍጥነት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባትን የሚያካትት ነው ብለዋል። ከዛም ባለፈ በጋራ ድርጅቶችን ማቋቋም እንዲሁም ትላልቅ ዎርክ ሾፖሽን ማሻሻል ጨምሮ በርካታ ስትራቴጂካዊ ስራዎች የሚሰራበት የጋራ ስምምነት መሆኑን…
Read More
ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመረቀች

ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመረቀች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያው ፕሬዚዳንት ውሊያም ሩቶ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኢል ኦማር ጊሌ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በተገኙበት የዓባይ ግድብ መርቀዋል። የኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ የምረቃ ሥነስርዓት ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓም ሲካሄድ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል። የዓባይ ግድብ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ 233 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደገ ሲሆን፤ ቦንድ በመግዛት፤ ስጦታ በመስጠት እና በሌሎች መንገዶች ህዝብ ትልቅ ተሳትፎ እንዳደረገ በስፋት ተግልጿል፡፡ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የህዳሴ ግድቡ መጠናቀቅም የኢትዮጵያን አቅም በሁሉም ዘርፍ የሚያሳግ እንደሆነም የተለያዩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ዓባይ ግድብ የሚገኘው በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ…
Read More
ንግድ ባንክ ለዲያስፖራዎች 50 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ንግድ ባንክ ለዲያስፖራዎች 50 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ንግድ ባንክ ለዲያስፖራው ማኀበረሰብ 50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አዘጋጅቼ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል። የባንኩ የብድር አገልግሎቱ ለኢንቨስትመንት፣ ለመኖሪያ ቤትና አውቶሞቢል ግዥ የቀረበ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአገር ውስጥ ለሚያካሄዱት የቢዝነስ እንቅስቃሴ፣ ለመኖሪያ ቤትና መሰል ፍላጎቶች የ50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልገሎት ተመቻችቷል ብለዋል፡፡ የብድር አገልግሎቱ በተያዘው የ2024/25 በጀት ዓመት ተፈጻሚ እንደሚሆንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ አገልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ለሚያቀርቡ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ቀልጣፋና ምቹ አሰራር እንደሚተገብርም አቶ አቤ አስታውቀዋል፡፡ ሙሉ ለሙሉ የመንግስት…
Read More
የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ አዲስ መመሪያ አወጣ

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በጋራ ኢንቨስትመንት ፈንዶች ላይ አዲስ መመሪያ አወጣ

በአሁኑ ወቅት በካፒታል ገበያ ሥር በተለያዩ ዘርፎች አገልግሎት ለመስጠት 10 ተቋማት የፈቃድ ማመልከቻ አስገብተው እየተጠባበቁ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታውቋል። በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ኃላፊ አቶ እንድሪስ ሰልማን፤ በኢትዮጵያ ያለው የካፒታል ገበያ ገና በማደግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ከጊዜ ወደጊዜ ፍላጎቱ እየጨመረ እንደሚመጣ ገልጸው፤ ያንን ፍላጎት ለመሙላት የሚያስችል ተጨማሪ አገልግሎት ሰጪዎች ገበያውን ሊቀላቀሉ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል። በዚህም ወደ 10 ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ደግሞ አንድ ሰው የኢንቨስትመንትና የሰነደ መዋዕለ ነዋይ አማካሪነትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የፈቃድ ማመልከቻ በማስገባት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ያመለከተው አካል በሙሉ ፈቃድ ይሰጠዋል ማለት እንዳልሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ "በተቀመጠው የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ መስፈርት መሰረት…
Read More
ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስማማ

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተስማማ

የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ማምረት የሚያስችል መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደርገው ጉዞ አንድ ሌላ እጥፋት ላይ በመድረሳችን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ደስ አለን!" ብለዋል። 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ይህ ሜጋ ፕሮጀክት በዓመት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ሲሆን፤ "ይህም ኢትዮጵያን ከዓለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ ያደርጋታል" ብለዋል። "ፕሮጀክቱ በሀገር…
Read More
ልማት ባንክ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መሰብሰቡን አስታወቀ

ልማት ባንክ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መሰብሰቡን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ወቅት፣ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ክምችት ማሰባሰቡን ይፋ አድርጓል። ይህ ባንኩ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አበድሮ የነበረውን ገንዘብ ከባለዕዳዎች መልሶ የሰበሰበው መጠን አፈጻጸም ከታለመለት ግብ በ5 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ51.6 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል። የባንኩ ዋና ትኩረት ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና እና ለሌሎች ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዚሁ በጀት ዓመት 18.0 ቢሊዮን ብር ገቢ በማሰባሰብ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተጠቅሷል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና፣ ማዕድን ማውጣት፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ኢንቨስትመንቶች የገንዘብ አቅርቦት የሚያመቻች መንግስታዊ ተቋም…
Read More
በኢትዮጵያ ከተመዘገቡ 6 ሺህ ቤት አልሚዎች ውስጥ ስራ ላይ ያሉት ከ400 አይበልጥም ተባለ

በኢትዮጵያ ከተመዘገቡ 6 ሺህ ቤት አልሚዎች ውስጥ ስራ ላይ ያሉት ከ400 አይበልጥም ተባለ

ከፌዴራልና ከክልል በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሪል እስቴት ልማት ዘርፍ ለመሳተፍ ፈቃድ የወሰዱና የተመዘገቡ 6 ሺሕ የሚሆኑ አልሚዎች ያሉ ቢሆኑም፤ በሥራ ላይ የሚገኙት ግን ከ400 እንደማይበልጡ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር አስታውቋል። የሪል እስቴት ዘርፉ ከአልሚዎች፣ ከገዢዎችና ከፋይናንስ ተቋማት ጨምሮ፤ በርካታ ችግሮች እና ተነሳሽነት ያልነበረበት እንደነበር የገለጹት፤ የማህበሩ ም/ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጀበል ጀማል ናቸው። ያለውን ችግር ለማስተካከልና በዘርፉ መተጋገዝ ካለና በጋራ መስራት ከተቻለ፤ የተሻለ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል በማመን የሪል እስቴት አልሚዎች ማሕበር መመስረት መቻሉንም አንስተዋል። ማሕበሩ ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በ29 አባላት መመስረት እንደቻለ አስታውሰው፤ አሁን ላይ ከ100 በላይ አባልትን በውስጡ መያዙን ገልጸዋል። አሁን ላይ እንደሀገር ከተመዘገቡት 6 ሺሕ…
Read More
የኬንያው ኪሲቢ ባንክ የኢትዮጵያን ባንክ 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ንግግር ጀመረ

የኬንያው ኪሲቢ ባንክ የኢትዮጵያን ባንክ 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ንግግር ጀመረ

ብሔራዊ ባንክ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅድ ህግ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም የኬንያው  ኬሲቢ ግሩፕ በኢትዮጵያ ባንክ ኢንቨስትመንት ለመስራት በንግግር ላይ መሆኑን ቢዝነስ ዴይሊ ዘግቧል፡፡ ባንኩ በሚቀጥሉት 18 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ የሚገኝን አንድ ባንክ 40 ከመቶ ድርሻን ለመግዛት ንግግር በማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል። ይሁንና ኬሲቢ ከየትኛው የኢትዮጵያ ባንክ ጋር ንግግር እንደጀመረ በዘገባው ላይ አልተገለፀም። ያም ሆነ ይህ የኬንያ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሰፊ የባንክ ስራዎችን በመስራት በኢትዮጵያ ተመራጭ ባንክ ለመሆን እቅድ ይዟል። ብሔራዊ ባንክ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ…
Read More