01
Sep
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ተቃውሞ አለኝ የምትለው ግብጽ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሳለች፡፡ ግብጽ በዛሬው ዕለት ለጸጽታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸችው ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለአምስተኛ ዓመት ውሃ ሙሌት አከናውናለች ይላል፡፡ በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስደተኞች እና ግብጻዊያን አርበኞች እንደተጻፈ የተገለጸው ይህ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የግብጻዊያንን ጥቅም በሚጻረር መልኩ የውሃ ሙሌት እያካሄደች ነው ብሏል፡፡ በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደል አቲ የተፈረመው ይህ የተመድ ደብዳቤ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን በፈረንጆቹ 2015 ላይ የተፈራረሙትን ስምምነት በመጣስ የግድቡ ውሃ ሙሌት በተናጠል ተከናውኗል፣ ይህም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የግድቡን…