ኢኮኖሚ

ኢሠማኮ መንግስት ለአደጋ ጊዜ በሚል ከተቀጣሪ ሰራተኞች ገንዘብ ለመሰብሰብ ማቀዱን ተቃወመ

ኢሠማኮ መንግስት ለአደጋ ጊዜ በሚል ከተቀጣሪ ሰራተኞች ገንዘብ ለመሰብሰብ ማቀዱን ተቃወመ

የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧቸው የተለያዩ አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” የሚሆን ገቢ እንዲሰበስቡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ባሳለፍነው ሳምንት ለፓርላማ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሳይወስን ገንዘብ ለመሰብሰብ አዲስ ረቂቅ ማስተዋወቁ ማንም አይጠይቀኝም ከሚል የመነጨ ነው ብሏል፡፡ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን በፓርላማ የፀደቀውን አዋጅ ሳያስተገብር ከሰራተኛው ላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ አዲስ ረቂቅ ማስተዋወቁ ማንም አይጠይቀኝም ከሚል የመነጨ ነውም ብሏል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን እንደ አዲስ እንዲቋቋም የታሰበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ለተቀጣሪ ሰራተኞች ራሱን የቻለ አደጋ ነው ብሎታል። ከሳምንት በፊት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ የቀረበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋትና ስራ…
Read More
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ። ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ እና ወጋገን ካፒታል አክሲዮን ማህበር ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ያገኙት የመጀመርያው የኢንቨስትመንት ባንኮች ሆነዋል። እነዚህ ባንኮች ራሳቸውን ችለው የተቋቋሙ የካፒታል ገበያ ስራ ብቻ የሚሰሩ የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው የተባለ ሲሆን በተጨማሪም ለአምስት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ ተሰጥቷል። ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች መካከልም ኢትዮ-ፊደሊቲ ሴኩሪቲስ አ.ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ (Securities Dealer) ፣ ኤች ኤስ ቲ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ. ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ፣ ኢኩዥን የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ኃ.የተ.የግ. ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ መሆናቸው ተጠቁሟል። ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች…
Read More
የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብር በጫና እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግሩ

የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብር በጫና እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግሩ

የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብርና ታክስ በተጨማሪ በሌሎች ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ተገለፀ የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ፎረም በከተማው ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ከባድ ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን ገልጿል። ፎረሙ የባለሀብቶችን ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። የባለአብቶች ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ለካፒታል እንደገለጹት፣ ባለሀብቶቹ ያላግባብ ድርጅቶቻቸው መታሸግ፣ መፍረስ፣ መነጠቅ (መቀማት)፣ ሥራ እንዲያቆሙ መደረግ፣ ያላመኑበትን ከፍተኛ ግብርና ታክስ ለማስከፈል ማስገደድ፣ የባንክ አካውንታቸው መታገድ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም እንዳይገቡ እየተደረጉ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ በስልክ ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረስ፣ የማያምኑበትን አሰልቺና ተደጋጋሚ መዋጮዎች መጠየቅ፣ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይከውኑ ማዋከብ፣ የብድር አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት እና የመሳሰሉት ችግሮች እየደረሱባቸው መሆኑን ሰምተናል ብለዋል። ይህን ተከትሎ ፎረሙ…
Read More
ኢትዮጵያ ስድስት የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ስድስት የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስድስት አዳዲስ የጭነት መርከቦችን ግዢ ሊፈፀም እንደሆነ አስታውቋል። 62 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት አልትራማክስ የደረቅ ብትን ጭነት መርከቦች በአጭር ግዜ ተገዝተው አገልግሎት እንደሚጀምሩ ድርጅቱ ገልጿል፡፡ የቀሪ አራት መርከቦች ግዥ በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ መርከቦቹን የምትገዛው የሀገሪቱን የገቢ ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ያግዛሉ በሚል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ 10 መርከቦች እንዳሏት ይነገራል። ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ መረከቧ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ባህር ዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት መርከቦች ለኪሳራ ዳርገውኛል በሚል መሸጡ ይታወሳል። በተሸጡት ሁለት መርከቦች…
Read More
የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለፀ፡፡ የግብር ዕዳ ያለባቸውና በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ዕዳቸውን ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆኑ 62 ግለሰቦችን ላይ ነው ትዕዛዙ የተላለፈው:: በዚህም ቢሮው በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 ለተቋሙ በተሰጠ ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዝርዝራቸውን ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡ ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የግብር ዕዳቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብር ከፋዮችን በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በአዲስ መልክ በማደራጀት ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል:: በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ…
Read More
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል። ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል። በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፣ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ አሳይተዋል። ይሁንና ባንኩ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔው በነበረበት በ12 በመቶ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች…
Read More
የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከ3 ሺህ በላይ ሠራተኞቹን አሰናበተ

የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከ3 ሺህ በላይ ሠራተኞቹን አሰናበተ

በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው ከሰም የስኳር ፋብሪካ፣ በክልሉ እየተከሰተ ባለው ለወራት የቀጠለ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይፋ ባደረገ በወሩ፣ ከ3,700 በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ ማሰናበቱ ታወቀ። በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በካምፕ የተጠለሉ 3,750 ቋሚና ጊዜያዊ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባልጠበቁት ሁኔታ ከሥራ ተሰናብተዋል። ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 123 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ከሰም ስኳር ፋብሪካ ከ10 ዓመት በፊት ነበር ስኳር ማምረት የጀመረው፡፡ በዓመት 260 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም የነበረው ይህ ስኳር ፋብሪካ በአዋሽ አካባቢ ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ስራ አቁሟል፡፡ በ20 ሺህ ሄክታር መሬት…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ 60 ሚሊየን ዶላር በነገው ዕለት በሁሉም ባንኮች ለጨረታ እንደሚቀርብ ባንኩ አስታውቋል። ባንኩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራምን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ክፍያ ሚዛን በተለይም የወጪ ንግድ፣ ሐዋላና የካፒታል ፍሰት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል ማሳየቱን ጠቅሷል። በተለይም ከቅርብ ወራት ወዲህ ወርቅን ወደ ውጭ የመላክ ብቸኛ ሥልጣን ላለው ብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ መጠን በመጨመሩ ምክንያት የባንኩ ዓለም አቀፍ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መጨመሩን ገልጿል። በመሆኑም ከባንኩ የወርቅ ግዥ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የገንዘብ አቅርቦት ዕድገት ለማገናዘብና በማዕከላዊ ባንኩ እጅ ካለው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከፊሉን ለግሉ ዘርፍ በመስጠት በገበያው ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል ባንኩ የተወሰነ…
Read More
ኢትዮጵያ በዓመት 400 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ እየላከች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በዓመት 400 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ እየላከች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በሰለጠነ የሰው ሀይል ዕጥረት ምክንያት ሰራተኞችን ወደ ውጭ ሀገራት መላክ እንዳልቻለች ተገለጸ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በዘረጋው የውጪ ሀገር የሥራ ስምሪት ገበያ ላይ ሂዶ ለመስራት ከሀገራት ከሚቀርበው ጥያቄ አንፃር፤ በከፍተኛ ሁኔታ የሚላኩ ዜጎች እጥረት መኖሩን ገልጿል፡፡ ከመዳረሻ ሀገራት በኩል በርካታ የሰለጠነ የሰው ሀይል ጥያቄን ለኢትዮጵያ እንደሚቀርብ የገለጹት፤ በሚኒስቴሩ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ፕሮጀክት ፅ/ቤት ኃላፊ ብርሀኑ አለቃ ናቸው፡፡ በብዛት የሰው ሀይል ጥያቄ ያለባቸው ሀገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ ሰው ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸውም ሀላፊው አንስተዋል። ጥያቄ ከሚያቀርቡ ሀገራት መካከልም ከመካከለኛው ምስራቅ ኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኩዌት፣ ሊባኖስ እና ጆርዳን ናቸው። እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራት ደግሞ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ እና ፖላንድ በከፍተኛ…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 62 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 62 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ።

በስመኝሽ ገብረወልድ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ 43.3 በመቶ ወይም 18.9 ቢሊዮን ብር እድገት አሳይቷል ብሏል። ገቢውም የእቅዱን 90.7 መሆኑን ተናግሯል። በዘንድሮ የበጀት ዓመት ስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም ነው ያለው። በዚሁ የስራ አፈፃፀም የግዜ ማዕቀፍ 6 ሚሊዮን ገደማ ደንበኞች አፍርቻለሁ ያለው ኩባንያው በአጠቃላይ የደንበኞቼ ቁጥርም 80.5 ሚሊየን ደርሰዋል ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም አገልግሎት ብዛት ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ዓለም አቀፉ የቴሌኮም አገልግሎት ድርጅት ወይም ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ (GSMA) ጥናት ተረጋግጧል ተብሏል። የደንበኛን ቁጥር ለመጨመር ከተሰሩት ስራዎች መካከል በግማሽ አመቱ 202 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተጠናቀው ወደ እንደገቡም ተገልጿል። በሞባይል ኔትዎርክ በተከናወኑ የፕሮጀክት…
Read More