19
Oct
ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የምትሰጠው የኢንሹራንስ አገልግሎት ሽፋን 0 ነጥብ 04 በመቶ ብቻ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የገጠር ፋይናንስ ክፍል የቡድን መሪ የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው መኮንን፤ ከ80 በመቶ በላይ የግብርና መር ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ በአርሶ አደሮቿ ምርት ላይ ለሚደርስ አደጋ የምትሰጠው የመድኅን ሽፋን ከአንድ በመቶ በታች ነው ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ለአርሶ አደሮቿ የምትሰጠው የግብርና መድኅን ሽፋን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው" ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤ "በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ 18 የኢንሹንስ ኩባንያዎች መካከል ለአርሶ አደሮች የኢንሹራንስ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ አግኝተው በመስራት ላይ የሚገኙት 4 ብቻ ናቸው" ብለዋል። ባለፉት 10 ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አጋር ድርጅቶች የኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለው ከ3…