nationalidethiopia

ብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ወደ 63 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

ብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎችን ወደ 63 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ሚያዝያ 2015 ላይ ነበር ብሔራዊ መታወቂያ በሙከራ ደረጃ መመዝገብ የጀመረችው፡፡ በ29 ከተሞች የተጀመረው ይህ ፕሮግራም ከታህሳስ 2014 ጀምሮ ከ70 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮ ነጋሪ ይህ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ ምን እንደሚመስል በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎችን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላትን አነጋግሯል፡፡ አቶ አማረ አሰፋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ አጣዬ ከተማ ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በ300 ኪሎ ሜትር በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ የድጅታል መታወቂያ ካሳለፈነው ሚያዝያ ወር ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን ገልጸው ከሁለት ወር በፊት የድጅታል አይዲው ታትሞ እጃቸው እንደገባ ነግረውናል፡፡ አሁን ላይ በአጣዬ ከተማ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች…
Read More