መነሻ ገፅ

በጋምቤላ ክልል ባለሀብቶች ህጻናትን በከብት እየለወጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል ባለሀብቶች ህጻናትን በከብት እየለወጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ብሄረሰብ ታፍነው ለባርነት የሚወሰዱ ህፃናት መኖራቸውን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው  የሕገ ወጥ ዝውውር ጽህፈት ቤት  አሰተባባሪ አቶ ኡቶው ቹሩ  እንደተናገሩት በዚህ መልኩ የሚወሰዱ ህፃናትን የማስመለስ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ህገወጥ የህፃናት ዝውውርን ማስቀረት አልተቻለም ብለዋል። በደቡብ ሱዳን በኩል ያለው ድንበር  ክፍት መሆን በክልሉ ያሉ እና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን በህገወጥ መልኩ ለመውሰድ አመቺ እንዳደረገው ገልፀው ባለሀብቶች ህፃናቱን በከብት የሚለውጡበት ሁኔታ መኖሩም ድርጊቱን እንዳይቆም ማድረጉን ተናግረዋል። አኙዋክ ብሔረሰብ ዞንን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ህፃናቱ እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከተወሰዱት ውስጥ በቅርቡ ሶስት ህፃናትን ማስመለስ መቻሉን የገለፁት አቶ ኡቶው በህይወት መኖራቸው ያልተረጋገጡ…
Read More
በኢትዮጵያ በቡና ላኪነት ለመሰማራት 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስያዝ ግዴታ ሆነ

በኢትዮጵያ በቡና ላኪነት ለመሰማራት 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስያዝ ግዴታ ሆነ

ከዚህ ቀደም የቡና ላኪነትን የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ይጠየቅ የነረበው የ1.5 ሚሊዮን ብር በ10 እጥፍ እንዲያድግ የተደረገው ዘርፉ በእውቀትና የተሻለ አቅም ባላቸው ሰዎች እንዲያዝ በማስፈለጉ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ይጠየቅ የነበረው ካፒታል 1.5 ሚሊየን ብር ነበር፤ ይህ ገንዘብ አሁን በአስር እጥፍ እንዲያግ በኢትዮጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን ማሻሻያ መቅረቡ ተሰምቷል። የሚጠየቀው ካፒታል አነስተኛ ሆኖ በመቆየቱ አትራፊ ነው በሚል ብቻ ብዙዎች የሚገቡበት ዘርፍ ሆኖ ቆይቷል የሚሉት የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ናቸው። ይሄ ደግሞ እዚሁ ሀገር ቤት በአቅራቢ እና ላኪዎች እንዲሁም ላኪዎች እና የውጭ ገዥዎች መካከል ችግሮች እንዲፈጠሩ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።  የቡና_ንግድ ሰዎች የተወሰነ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ14 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ14 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 9 ወራት 14.5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ13 በመቶ እድገት እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡ አየር መንገዱ በዘጠኝ ወር ውስጥ ያገኘው ገቢ 5.6 ቢሊዮን ዶላር መሆኑንን የተናገሩት አቶ መስፍን ጣሰው ገቢውም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡ በጊዜ ማዕቀፍ 10 አዳዲስ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድን መቀላቀላቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ኤርባስ A350-1000 መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ በዘጠኝ ወሩ ውስጥ አራት አዳዲስ የበረራ መዳረሻዎችንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መክፈቱን ጠቅሷል፡፡ አየር መንገዱ የፊታችን እሁድ ጁን 1, 2025 ከአዲስ አበባ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ሻርጃህ ከተማ…
Read More
የአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

የአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

57 በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት ለከፍተኛ የእዳ ችግር መጋለጣቸው ተገልጿል። እነዚሁ ታዳጊ ሀገራት በተያዘው ዓመት ብቻ ከ 80 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጪ እዳ እንዲከፍሉ ይጠበቃል በአፍሪካ የሕዝብ ዕዳ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት አስታውቋል ። እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ በአህጉሪቱ ከሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት መካከል 57% የሚሆኑት በዕዳ ችግር ውስጥ ገብተዋል ወይም ከፍተኛ የዕዳ ስጋት ላይ ይገኛሉ። ይህንን አኃዝ የገለጹት የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፓቲ ማርቲን በአዳስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘዉ 51ኛዉ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ዓመታዊ ኮንፍረንስ እና ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ላይ ሲሆን :- በዚህ ንግግራቸው የዕዳው ጫና መጨመር ዋና ዋና መንስኤዎች የዓለም አቀፍ የገበያ መዋዠቅ እና…
Read More
አሜሪካ ፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም እቅዳቸውን እንዲያሳውቁ ጠየቀች

አሜሪካ ፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም እቅዳቸውን እንዲያሳውቁ ጠየቀች

አሜሪካ ዛሬ አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ በኩል ለፌዴራል መንግሥት እና ለታጣቂዎች መልዕክት አስተላልፋለች። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት በመላው ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለጉዳት የዳረጉ ግጭቶች ሰላማዊና ትክክለኛ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። አምባሳደሩ፥ ለታጣቂ ኃይሎች እና ለፌደራል መንግስት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝብን እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርበዋል። " ጦርነቱን ማቆም፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መርዳት እና ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ እና የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል። " በትጥቅ ትግል ስም የሚፈጸሙ ህገወጥ እና የኃይል እርምጃዎች ሊቆሙ ይገባል " ብለዋል። አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በመልዕክታቸው ለፋኖ ፣ ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) እና ለፌደራል መንግስት የተናጠል መልዕክት…
Read More
መንግሥት ሐኪሞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኢሰመኮ አሳሰበ

መንግሥት ሐኪሞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኢሰመኮ አሳሰበ

በሕክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በር እንዳይከፍቱ ትኩረት እንዲሰጣቸውም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሕክምና ባለሙያዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ያሳስባል። ኢሰመኮ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስ ሰጥተናል ያሉት የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ በመንግሥት እና በሕክምና ባለሙያዎች በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃዎች በመከታተል ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት ኢሰመኮ…
Read More
የገቢዎች ሚንስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ649 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

የገቢዎች ሚንስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ649 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

ሚኒስቴሩ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 649 ቢሊዮን ብር ሰብስቤያለሁ ብሏል ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ 74 በመቶ ወይም የ279 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡ ከተሰበሰበው ገቢ 345.9 ቢሊየን ብሩ ከታክስ የተገኘ ሲሆን ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 307.2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገልጿል። ገቢው በመቶ ቢሊዮኖች ከአምናው ከፍ ያለበት ምክንያት ግን በሪፖርቱ አልተብራራም፡፡ በሌላ በኩል ህገ-ወጥ ንግድ ፣ ገቢን መደበቅ ፣ ግብይትን ያለ ደረሰኝ መከወን ፣ ግብር ስወራና ታክስ ማጭበርበር አሁንም ፈተና ሆነውብኛል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡ ተሰውሮብኝ ነበር ያለውን ገቢ ለማግኘትም በድንገተኛ ፍተሻ ፣ በሒሳብ ምርመራ ወይም ኦዲትና መሰል ስራዎች የህግ ማስከበር ስራ ሰርቻለሁ ብሏል፡፡ በዚህም 7 ሺህ 583 የሒሳብ…
Read More
በካቻ የነዳጅ ክፍያ መክፈል ተጀመረ

በካቻ የነዳጅ ክፍያ መክፈል ተጀመረ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ክፍያ ሰነድ አውጪ የሆነው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አሽከርካሪዎች ካቻን በመጠቀም በቀላሉ የነዳጅ ክፍያን የሚከፍሉበትን አገልግሎት በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል። አገልግሎቱም ደንበኞች የካቻን መተግበሪያ በመጠቀም ፣ በ“Push USSD Notification” እንዲሁም በQR ኮድ ስካን በማድረግ በቀላሉ የነዳጅ ክፍያን መፈፀም የሚያስችል ሲሆን የካቻ ደንበኛ ያልሆነ ማንኛውምአሽከርካሪ መተግበሪያውን ከፕሌይስቶር ወይም አፕስቶር በማውረድ ከማንኛውም ባንክ ወደ ካቻ ገንዘብ በማስተላለፍ  ወዲያውኑ ክፍያ መፈፀም እንደሚያስችል ተገልጿል። "የዛሬው ምርቃት ካቻ ለማህበረሰባችን ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ፉይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ለሚያደርገው ጉዞ አንድ እርምጃ የሚያግዘን ነው"ያሉት የካቻ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሀም ጥላሁን "በቀጣይም ካቻ በአሽከርካሪዎች ላይ ያለውን የፋይናንስ ጫና…
Read More
ኢትዮጵያ የአልኮል መጠጦችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጩ የሚከለክል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የአልኮል መጠጦችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጩ የሚከለክል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች

የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ ተዘጋጅቷል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሰልጣን የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ አዘጋጅቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የአልኮል ምርቶችን እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ በህግ ማገዷ ይታወቃል። የአልኮል አምራች ተቋማት በአሁን ሰዓት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም፤ ምርታቸውን እያስተዋቁ እና ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች እየደረሱ ነው ተብሏል። ከእነዚህ መካከልም የማህበራዊ ሚዲያ በብዛትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተነግሯል። ይህንን እየተስፋፋ የመጣው በማህበራዊ ሚዲያ የአልኮል ማስታወቂያን በተቻለ መጠን ለመገደብ ታስቦ፤ የህግ ማዕቀፍ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚኝ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፍሬሰላም ዮሴፍ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ…
Read More
ብሔራዊ ሎተሪ 50 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሎተሪ ይፋ አደረገ

ብሔራዊ ሎተሪ 50 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሎተሪ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደገለፀው ይህ ዘመናዊ ሎተሪ ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ በዲጅታል መላ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብሏል። በዲጂታል ሎተሪ ለረጅም ዓመታት በመፋቅ እድለኛ የሚያደርጉት የፈጣን እና የቢንጎ ሎተሪዎችም በዲጅታል መንገድ እንደተካተቱ ተገልጿል።ከሀምሳ ሚሊዮን ብር ሽልማት አንስቶ በርካታ የጨዋታ አማራጮችን የቀረበበት  ሲሆን በስምንት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ይህንን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር  እየሰራ መሆኑን ገልጿል። አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዲጅታል ሎተሪ በተጨማሪ በሃምሳ ሺህ ብር ሽልማት የከፈተውን የእድል በር ወደ ሃምሣ ሚሊየን ብር ከፍ ለማድረግ እንደበቃም ተናግሯል። ብሔራዊ ሎተሪ በየጊዜው አዳዲስ የሎተሪ እድኮችን ለደንበኞቹ ያስተዋወቀ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት አድማስ…
Read More