15
Sep
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ከተፈተኑ 586 ሺህ ተማሪዎች ውስጥ ያለፉት 49 ሺህ ገደማ ህሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 585 ሺህ 882 ተማሪዎች መካከል 48 ሺህ 929 ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የፈተና ውጤቱን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት ፈተና ከወሰዱ 585 ሺህ 882 ተማሪዎች መካከል 48 ሺህ 929 ከ50 በመቶ በላይ ያስመዘገቡ በመሆናቸው ወደ ዩንቨርስቲ ይገባሉ ብለዋል። ፈተናቸውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። እንደ ፕሮፌሰሩ ገለፃ በዘንድሮው ዓመት…