Blog

ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ለኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር አዲስ ሀላፊ ተሾመለት

ዳንኤል ኃ/ሚካኤል የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተደርገው ተሾመዋል፡፡ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር (ኢዲአር) ቺፍ ቴክኒካል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ዳንኤል ኃ/ሚካኤል ከሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾመዋል። የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ለኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት አብዲ ዘነበ ምትክ ዳንኤልን ኃ/ሚካኤልን ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዲሆኑ መድበዋል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተጓዦችና የጭነት አገልግሎት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ይታወሳል። ማኅበሩ በየቀኑ ከ700 እስከ 1 ሺህ ሰዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ155…
Read More
ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች አስመረቀች

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች አስመረቀች

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በትናትናው እለት አስመርቃለች። በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) በትናንትናው ዕለት ተማሪዎቹን ያስመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ መካከልም በአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎቹ ይገኙበታል። በቻይና የኢትዮጵያ ኤማባሲ ተወካዮች ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ምርቃት ላይ መሳተፋቸውንም ኤምባሲው አስታውቋል። “በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU በቻይና ውስጥ ብቸኛው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል የሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ ትናንት ከተመረቁት መካከል የመጀመሪያው ዙር የአማርኛ ተማሪዎች ይገኙበታል ብሏል ኤምባሲው ባወጣው መረጃ። ኤምባሲው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠቱን አመስግኖ፤ “ይህ የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያጠናክራል” ብሏል። የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ መማሪያ…
Read More
በአማራ ክልል ደብረሲና እና አዴት ከተሞች ከ27 በላይ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ደብረሲና እና አዴት ከተሞች ከ27 በላይ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች በቀናት ልዩነት “የመንግሥት ኃይሎች” ቤት ለቤትና መንገድ ላይ ‘ሰላማዊ ሰዎችን’ መግደላቸውን የዐይን እማኞችና ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቶቹ ሰኞ ሰኔ 17 እና ረቡዕ ሰኔ 19፤ 2016 ዓ/ም መፈጸማቸው የተነገረ ሲሆን፤ በጥቃቶቹም ከ27 በላይ ንጹሃን ሰዎች እንደተገደሉ ተገልጿል። በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና አራት የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በከተማዋ ‘አጋም በር መገንጠያ’ በተባለ ሰፈር ጥቃቱ ምሽት 11፡30 አካባቢ እንደተፈጸመ የተናገሩ አንድ ከጥቃቱ የተረፉ እማኝ፤ በጥቃቱ በአብዛኛው ማዳበሪያ ለመውሰድ…
Read More
የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

የቀድሞው ማንችስተር ዩናይትድ ኮኮብ ልዊስ ናኒ ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው

ፖርቹጋላዊው እግር ኳስ ተጫዋች ልዊስ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ገልጿል፡፡ ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ተጨዋች ሉዊስ ናኒ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ባሰራጨው ቪዲዮ አስታውቋል፡፡ ናኒ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚመጣው የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ ለሚገኘው መቻል እግርኳስ ክለብ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሆን ተገልጿል። ናኒ ባስተላለፈው አጭር የቪዲዮ መልዕክትም " ሰላም ኢትዮጵያውያን ሰማንያኛ አመቱን ከሚያከብረው መቻል ግብዣ ስለቀረበልኝ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል። ለእኔ ልዩ ቦታ ያላትን ኢትዮጵያ ለመጎብኘት ጓጉቻለሁ በቅርቡ እንገናኝ" ሲል ተደምጧል። መቻል እግር ኳስ ክለብ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር የተቋቋመ ቡድን ሲሆን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተወዳደረ ይገኛል፡፡ ክለቡ…
Read More
ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር አራተኛ ሆና አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር አራተኛ ሆና አጠናቀቀች

በካሜሩን አስተናጋጅነት የተካሄደው የመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል፡፡ በካሜሩን ዋና ከተማ ዱዋላ አስተናጋጅነት ከ27 ሃገራት በላይ የተውጣጡ 2500 አትሌቶች ላለፉበት 6 ቀናት ሲሳተፉበት የነበረው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቋል። በዚህ ውድድር ለይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5 ወርቅ፣ 4 የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝቷል፡፡ ኢትዮጵያጵያ በውድድሩ ላይ 68 አትሌቶችን በ19 የአትሌቲክስ የውድድር አይነቶች ላይ የተሳተፈች ሲሆን ከናይጀሪያ በመቀጠል አራተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ፋንታዬ በላይነህ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ፣ንብረት መላክ በ10ሺ ሜትር ወንዶች ፣ምስጋና ዋቁማ በወንዶች በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ፣    ስንታየሁ ማስሬ በሴቶች በ20 ኪሎ ሜትር…
Read More
አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ 150 ሺህ ዶላር የሚያወጡ ድጅታል ብሬሎችን ተረከበ

አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ 150 ሺህ ዶላር የሚያወጡ ድጅታል ብሬሎችን ተረከበ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዘመናዊ ዲጂታል ብሬሎችን መረከቡን ገልጿል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኮሪያው ሴሎም ኢንተርናሽናል ኮኦፕሬሽን ኤጀንሲ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት መሰረትም እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ዶላር የሚያወጡ 30 ዲጂታል ብሬሎችን እንደተረከበ አስታውቋል፡፡ ዩንቨርሲቲው እንዳስታወቀው በቀጣይ ደግሞ ተመሳሳይ ቀሪ 30 ብሬሎችን በድጋፍ እንደሚረከብ ገልጿል። ይህ ዘመናዊ መሳሪያ ማየት የተሳናቸው  የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ከወረቀት ብሬል ተላቀው በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚረዳ ሲሆን፤ ከተለያዩ ዳታቤዞችም ጥናታዊ ጽሑፎችን ያለምንም ክፍያ አውረደው መጠቀም ያስችላቸዋል ተብሏል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱ መሰረት ለዲጂታላይዜሽን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አዲስ አበባ…
Read More
ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገለጸ

ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገለጸ

ዋና መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት እንዳልሰጠ አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የአገሪቱን የመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት በማድረግ የደንበኞቹን ነፃነት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ ተቋሙ እንዳለው በፍርድ ቤት አማካኝነት ካልታዘዘ በስተቀር ማንኛውንም የደንበኞቹን መረጃ ለሌላ ሶስተኛ አካል አሳልፎ እንደማይሰጥ ገልጿል፡፡ ድርጅቱ እስካሁን የደንበኞቹን መረጃ እንዲሰጥ ከመንግስት ጥያቄ እንዳልቀረበለት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አካል አሳልፎ እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳልደረሰውም በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ የድርጅቱ እህት ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ በሚል ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ህጋዊ ፍቃድ ከተቀበለ ከአንድ ዓመት በኋላ ስራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት ወደ…
Read More
በሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 አለፈ

በሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 አለፈ

በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 ተሻግሯል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ሳዑዲ አረቢያ ገልጻለች፡፡ በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺህ 300 መሻገሩን ሳዑዲ አረቢያ አስታውቃለች። እስካሁን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የ10 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ 658ቱ ግብጻውያን ናቸው ተብሏል። 150 ሺህ ሃጃጆችን የላከችው ፓኪስታን 58 ዜጎቿ ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጋለች። ከ240 ሺህ ኢንዶኔዥያውያን ሃጃጆች መካከልም 183ቱ መሞታቸውን የሀገሪቱ የሃይማኖቶች ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የሱዳን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ህንድ፣ ዮርዳኖስ፣ ማሌዥያና ኢራን ዜግነት ያላቸው ሃጃጆችም ህይወታቸው ማለፉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ከዚህ ውስጥ አምስቱ ኢትዮጵያዊን እንደሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ ሟቾች ያለፈቃድ…
Read More
በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ምርጫ መካሄድ ጀመረ

በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ምርጫ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች በዛሬው ዕለት ምርጫ እየተካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። ዛሬ እየተካሄደ ባለው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይም 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ መሆኑን ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተካሄደ መሆኑንም ነው ቦርዱ ያስታወቀው። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች አንዱ በአፋር ክልል የሲሆን፤ በክልሉ 4 ዞኖች፣ በ9 የምርጫ ክልሎች እና በ388 የምርጫ…
Read More
በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ሀይሎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ከወሰነበት ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት አልፎታል፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ለ10 ወራት የዘለቀ የአስቸኳይ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ካሳለፍነው ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀመሮም የአዋጁ ጊዜ ቢያበቃም ክልሉ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛ እና ቀወት ወረዳዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ሬዲዮ…
Read More