Blog

በኢትዮጵያ የባንኮች የገንዘብ ዝውውር ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የባንኮች የገንዘብ ዝውውር ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በባንክ የሚካሄድ አጠቃላይ የገንዘብ ዝውውር ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ማኅበር "ባካሄድኩት ጥናት አረጋግጫለሁ" ብሏል። በማኅበሩ ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ ናስር የኑስ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ በተለይ ከ2012 ዓ.ም. መጨረሻ ወራት አንስቶ፣ በይበልጥ ደግሞ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ የገንዘብ ዝውውር (ትራንዛክሽን ባንኪንግ) አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥር እየቀነሰ ነው። ለዚህ የገንዘብ ዝውውር መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ያሏቸውን ጉዳዮች የጠቀሱት የምጣኔ ሃብት ተመራማሪው፤ የዜጎች የገቢ ማሽቆልቆል፣ አልፎ አልፎ የሚታዩ ግጭቶችና ጦርነቶች እልባት አለማግኘት፣ የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር፣ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ችግር እንደሆኑ ዘርዝረዋል። ተመራማሪው ይህንን እያሽቆለቆለ ያለውን የገንዘብ ዝውውር ለማነቃቃት ባንኮች ሊተገብሯቸው ይገባል ካሏቸው የመፍትሔ እርምጃዎች መካከል፤ ባንኮች ለገንዘብ ዝውውር…
Read More
ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ሆኑ

ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ሆኑ

የዓለም አትሌቲክስ በሁለቱም ፆታ የ2025 የዓመቱ የጎዳና ላይ ምርጥ አትሌት ዕጩዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህም ኢትዮጵያ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ እና ዮሚፍ ቀጄልቻን በዓመቱ በሁለቱም ፆታ ምርጥ ብቃት ካሳዩ አምስት አትሌቶች መካከል ተብለው እጩ ሆነዋል። በሴቶቹ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ከኬንያውያኑ አትሌቶች ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና አግኔስ ንጌቲች፣ ለኔዘርላንድስ ከምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን እና ከስፔናዊቷ ማሪያ ፔሬዝ ጋር ምርጥ አምስት ውስጥ መግባት ችላለች። በወንዶቹ ደግሞ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ከብራዚላዊው አትሌት ካይኦ ቦንፊን፣ ካናዳዊው አትሌት ኢቫን ዱንፊ፣ ኬንያዊው አትሌት ሳባስቲያን ሳዌና ከታንዛኒያዊው አልፎንስ ሲምቡ ጋር ምርጥ አምስት መግባት ችሏል። በለንደን ማራቶን አሸናፊ የነበረችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በውድድር ዓመቱ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ…
Read More
በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ

በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳስበዋል። ችግሩን በሐይማኖት አባቶች እና በሽማግሌዎች ብቻ ለመፍታት ከመጣር ይልቅ፣ በድርድር እና በእውነተኛ አካታች ውይይት መፍታት እንደሚገባም የፓርቲዎቹ አመራሮች ጥሪ ማቅረባቸውን አሀዱ ሬዲዮ ዘግቧል። የአንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሲሳይ ደጉ፤ "መንግሥት እና አማራ ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች ዋናው ሀገራዊ ምክክር ከመካሄዱ በፊት ያለው የጸጥታ ችግር በሰላም መፈታት አለባቸው" ብለዋል። አቶ ሲሳይ የፌዴራል መንግሥት "ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርቤያለሁ" የሚለውን ቃሉን ተግባራዊ እንዲያደርግ፤ ጥረት እየተደረገ ከሆነም መንግሥት ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ይህንን ሀሳብ የሚጋሩት የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ የፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ሐድጉ በበኩላቸው፤…
Read More
የቪዛ ጊዜያቸውን ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጡ

የቪዛ ጊዜያቸውን ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጡ

በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር ተመልሰዋል አለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ እየተሰራ ነው፡፡ በዘርፉ በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ሀገራዊ አቅም መጠናከሩን አመልክተዋል፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ በተካሄዱ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባዔዎች የተሳተፉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ያለምንም እንከን መስተናገዳቸውን ጠቅሰዋል። በቪዛ አገልግሎት ወደ 188 ሀገራት የመዳረሻ (ኦን አራይቫል ቪዛ) ተጠቃሚዎች ሆነዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ÷ ይህም የ24 ሰዓት የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት ያለው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የተለያዩ የማሻሻያ ርምጃዎች መወሰዳቸውን እና በዚህም በሕገ ወጥ ሰንሰለት የተሰማሩ 26…
Read More
የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 24 እንዲሆን ቀረበ

የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 24 እንዲሆን ቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል። የምርጫ ውጤት ለህዝብ ማሳወቂያ ቀን ደግሞ ሰኔ 3 ቀን እንደሚሆንም ቦርዱ አስታውቋል። ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አድርጓል። ከ60 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት ላይ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ የጦፈ ውይይት መደረጉ ተገልጿል። መገናኛ ብዙሃን ባልተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳን ለፓርቲዎች ለውይይት አቅርቧል። ለውይይት በቀረበው የጊዜ ሰሌዳው መሰረትም ህዳር ወር ውስጥ በምርጫ መወዳደር የሚፈልጉ…
Read More
ኢትዮጵያ ከቻይና ያለባትን ዕዳ ወደ ዩዋን እንዲቀየር ጠየቀች

ኢትዮጵያ ከቻይና ያለባትን ዕዳ ወደ ዩዋን እንዲቀየር ጠየቀች

ኢትዮጵያ ለቻይና መንግሥት የምትከፍለውን ቢያንስ 5.38 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በከፊል ወደ ቻይና ገንዘብ (ዩዋን) ለመቀየር ከቤጂንግ ጋር ውይይት መጀመሯ ተዘግቧል። ይህ እርምጃ ቀደም ሲል ኬንያ ያደረገችውን በመከተል፣ ቻይና የገንዘብ ምንዛሪዋን ዓለም አቀፋዊ የማድረግ ጥረቷን የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል። ብሉምበርግ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ እዮብ ተካለኝ ባለፈው ወር ወደ ቤጂንግ ባደረጉት ጉብኝት ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ እና ከቻይና ሕዝብ ባንክ ጋር ለዚህ እምቅ የዕዳ ልውውጥ ውይይት መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ገዥው ይህንን የገለጹት አርብ ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው። ሀገሪቷ ዕዳውን በዩዋን መክፈል የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ያለውን…
Read More
ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን ከኤርትራ መረከቧ አይቀሬ መሆኑን ገለጸች

ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን ከኤርትራ መረከቧ አይቀሬ መሆኑን ገለጸች

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ኮሞዶር ተገኝ ለታ እንዳሉት የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰላምና መረጋጋት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። ምክትል አዛዡ ይህን የተናገሩት ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በመከላከያ ዋር ኮሌጅና በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትብብር “የሁለቱ የውሃ ሥርዓቶችና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ነፃነት፣ የዓባይና የቀይ ባሕር ትስስር እና የአፋር ክልልን ስትራቴጂካዊ ሚና መዳሰስ” በሚል ርዕስ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ኮሞዶር ተገኝ ለታ የኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆን በሀገሪቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሊኖረው የሚችለው ኢኮኖሚዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ መዘዝን መረዳት ተገቢ መሆኑንም አጽኖት ሰጥተው…
Read More
ከ18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች  አርሶ አደሮችን የሚያገለግሉት 4 ብቻ ናቸው ተባለ

ከ18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አርሶ አደሮችን የሚያገለግሉት 4 ብቻ ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የምትሰጠው የኢንሹራንስ አገልግሎት ሽፋን 0 ነጥብ 04 በመቶ ብቻ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የገጠር ፋይናንስ ክፍል የቡድን መሪ የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው መኮንን፤ ከ80 በመቶ በላይ የግብርና መር ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ በአርሶ አደሮቿ ምርት ላይ ለሚደርስ አደጋ የምትሰጠው የመድኅን ሽፋን ከአንድ በመቶ በታች ነው ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ለአርሶ አደሮቿ የምትሰጠው የግብርና መድኅን ሽፋን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው" ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤ "በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ 18 የኢንሹንስ ኩባንያዎች መካከል ለአርሶ አደሮች የኢንሹራንስ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ አግኝተው በመስራት ላይ የሚገኙት 4 ብቻ ናቸው" ብለዋል። ባለፉት 10 ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አጋር ድርጅቶች የኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለው ከ3…
Read More
ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሶስት ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር እንደገለጸው ባለፉት ሦስት ወራት ለውጭ ገበያ ካቀረበቻቸው ምርቶች 2 ነጥብ 48 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን አስታውቋል። ሚንስቴሩ በበጀት ዓመቱ ሩብ ወራት ጥራጥሬንና የቅባት እህሎችን ከመሳሰሉ ምርቶች 149 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጿል። በተያዘው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ዘርፉ ለማግኘት የታቀደው አጠቃላይ ገቢ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው ገቢ የ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አለው። ከፍተኛ ገቢ ካስገኙ ምርቶች መካከል ቡና ሲሆን 762 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገልጿል። ገቢው የተገኘው፣ 113 ሺህ 542 ቶን ቡና በመላክ ነው የተባለ ሲሆን ከ151 ሺሕ 969 ቶን በላይ ቡና በመላክ፣ 622 ነጥብ 5…
Read More
ኢትዮጵያ ስታካሂደው የነበረው የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ዕዳ ድርድር ተቋረጠ

ኢትዮጵያ ስታካሂደው የነበረው የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ዕዳ ድርድር ተቋረጠ

ኢትዮጵያ የ 1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር ስታደርግ የነበረዉ ድርድር ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በ2024 ዓ.ም. ዋናው ዕዳ የሚከፈልበት የአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ዕዳዋን ለማዋቀር  ያደረገው ወሳኝ ጥረት ከቦንድ ባለቤቶች ተወካዮች ጋር ሲያደርገው የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ለዚህ ብድር በየዓመቱ 6.625% ወለድ ለመክፈል መስማማቷ ይታወቃል። የገንዘብ ሚኒስትር እንዳስታወቀው በመስከረም 15 እና ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም መካከል የተካሄደው ውይይት በሁለቱ ወገኖች የቀረቡትን የመጨረሻ የዕዳ ማዋቀር ሃሳቦች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ አልተቻለም። ሚኒስቴሩ ድርድሩ በዚህ ጊዜ ሳይሳካ ቢቀርም፣ "ሰፊ መሻሻል" መመዝገቡን ገልጾ፣ ውይይቱ ወደፊት እንደሚቀጥል ተስፋውን አጠናክሯል። ሁለቱም ወገኖች ለአዲሱ ቦንድ እትም ዋናውን ዕዳ በ15%…
Read More