12
Feb
37ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በውድድሩ አዘጋጅ ሀገር ኮቲዲቯር አሸናፊነት ተጠናቋል። ጥር 3 ቀን ተጀምሮ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ፍጻሜውን ያገኘው ይህ ውድድር ናይጀሪያ እና ኮቲዲቯር ለዋንጫ ተጫውተዋል። ናይጀሪያ በመጀመሪያው አጋማሽ በአምበሏ ኢኮንግ ጎል ቀድማ ጎል ያስቆጠረች ቢሆንም ኬሲ እና ሀለር ኮቲዲቯርን የዋንጫ ባለቤት ያደረጉ ጎሎችን አስቆጥረዋል። ይህን ውድድር ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛ እንዲሁም ዲሞክራቲክ ኮንጎ አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል። በዚህ ውድድር ላይ የኮቲዲቯር አሰልጣኝ ኤምሬ ፋኤ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ሲሞን አዲንጋራ ምርጥ ኮከብ ወጣት ተጫዋች ናይጀሪያዊው ዊሊያም ኢኮንግ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች፣ የ34 ዓመቱ የኢኳቶሪያል ጊኒው ኤምሊያኖ ኑስ በአምስት ጎሎች ኮከብ ግብ አግቢ እንዲሁም ሮንውን ዊሊያምስ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን ተመርጠዋል።…