23
Aug
የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ ልማት፣ ሴቶች እና እኩልነት ሚኒስትር አኔሌሴ ዶድስ በኢትዮጵያ ጉብኘት አድርገዋል፡፡ ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ በነበራቸው የአንድ ቀን ጉብኝታቸው ከኢትዮያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር እንደተወያዩ ተገልጿል፡፡ የዩኬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉብኝቱን አስመልክቶ በድረገጹ ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ግጭቶች እንዳሳሰቡት አስታውቋል፡፡ መግለጫው አክሎም በሁለቱ ክልሎች ያሉ ግጭቶች ንጹሃን እየጎዱ ነው ያለ ሲሆን የግጭቱ ሁሉም ተሳታፊዎች አለመግባባቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል፡፡ ዩኬም ለኢትዮጵያ ሰላም፣ ደህንነት እና ኢኮኖሚ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልግ ሚኒስትሯ ከአምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር በነበራቸው ውይይት ወቅት መነሳቱም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ዩኬ የዓለም አቀፍ ልማት እኩልነት እና ሴቶች ሚኒስትርን ወደ ኢትዮያ የላከችው…