18
Aug
ከሰሞኑ የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህር ዳር ከተማ የሰባት ዓመት እድሜ ያላት ህጻን ሔቨን የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ከተፈጸመባት በኋላ ህይወቷ እንዳለፈ የህጻኗ እናት ለተለያዩ ሚዲያዎች ተናግራለች፡፡ በርካቶችን ያስቆጣው ይህ ድርጊት ወንጀሉን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ በተፋጠነ ምርመራ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ የ25 ዓመት እስር እንደተላለፈበትም ተገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎ ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ላይ የተላለፈበት ውሳኔ በቂ ካለመሆኑ በላይ ግለሰቡ ፍርዱ እንዲቀነስለት ይግባኝ ማለቱም ተነስቷል፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተፈጸመ የተገለጸው ይህ ወንጀል ጉዳዩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ሲሆን ተቋማት ሳይቀር በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫዎችን በማውጣት ላይ ናቸው፡፡ የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር በጉዳዩ…