22
Aug
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የነፍሰጡሮች የቁንጅና ውድድር በመስከረም ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ ። ታዋቂ ኢቪንትስ ከጤና ሚኒስቴር እና ከብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ጋር በጋራ ያዘጋጀውን ውድድር በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የውድድሩ አላማ በሀገሪቱን በስፋት እየተስተዋለ ስለሚገኘው የእናቶችን በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ህይወት ማለፍን አስመልክቶ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል። ነፍሰ ጡርነት ውበት መሆኑን ለሌሎች በማስገንዘብ እና የጤና ክትትል የማያደርጉ ነፍሰ ጡር እናቶችን ክትትላቸውን እንዲያደርጉ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ ለማሳየት መሆኑም ተመላክቷል። በዚህ የቁንጅና ውድድር 15 ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች እንደየደረጃቸው ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል። በውድድሩ ለመውለድ የተዘጋጁ ነፍሰ ጡሮች በዲዛይነሮች በተዘጋጁ ቅንጡ የነፍሰጡር አልባሳት ተውበው ይታያሉ ተብሏል። በቁንጅና…