06
Apr
የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በግዴታ ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ በመጀመሩ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፤ በክልሉ ልዩ ኃይል እና በፌዴራል የጸጥታ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ፡፡ የክልሉን ልዩ ኃይል ያለ በቂ ዝግጅት፣ ውይይት፣ የጋራ መግባባትና መተማመን ሳይደረስ በድንገት እና ያለበቂ የጸጥታ ዋስትና ለማፍረስ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄደበት ያለው መንገድ ኃላፊነት የጎደለው መሆኑን አብን አስታውቋል፡፡ ጉዳዩ በአማራ ክልል ብቻ ሳይወሰን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አለመረጋጋት የሚፈጥር፣ ክልሉን እና ኢትዮጵያን ወደ ሌላ የቀውስ አዙሪት የሚከት አደገኛ አካሄድ መሆኑን አብን ለፌዴራሉ መንግሥትና ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳስቧል፡፡ በመሆኑም፣ የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔውን በአፋጣኝ እንዲቀለብስ እና ከአማራ…