12
Aug
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ጋር በተያያዘ በመካከላቸው የተፈጠረዉን ዉጥረት ለመፍታት ሁለተኛ ዙር ድርድራቸውን በአንካራ ጀምረዋል፡፡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ንትርክ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር በስልክ መምከራቸውም ተሰምቷል፡፡ የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን ከሶማሊያ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር በስልክ መምከራቸዉ ተዘግቧል። በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት በማጉላት አንካራ ፥ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረቷን እንደምትቀጥል የቱርክ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በኤክስ ገጹ ላይ ጽፏል። በዛሬዉ እለት በቱርኪዬ ርዕሰ መዲና አንካራ ከሚካሄደው ሁለተኛ ዙር የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ ድርድር ውጥረቱን ለማርገብ ተጨባጭ ውጤት ይጠበቃል ብሏል። መሪዎቹ በስልክ ዉይይታቸዊ በሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በአህጉራዊ እና…