20
Apr
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋሸንግተን በተካሄደው የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ትገኛለች፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናትም እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት የጠየቀች ሲሆን ተቋሙ ግን ብድር ለኢትዮጵያ ከመስጠቱ በፊት የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡ ከተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ኢትዮጵያ የብሯን የመግዛት አቅም እንድታዳክም የሚለው ሲሆን ይህ ጉዳይ እስካሁን አጨቃጫቂ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያ እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት ድርድር ሲያደርጉ ከአንድ ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን በየጊዜው ሳይስማሙ በመለያየት ላይ ናቸው፡፡ ከአንድ ወር በፊት የዓለም ገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ወደ አዲ አበባ መጥተው…