24
Jan
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የቁርአን እና አዛን ውድድር ጥር 25 እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቁርኣንና የአዛን ውድድር ሽልማት 2ኛ ዙር 2025 ውድድርን ምክንያት በማድረግ በርካታ ሀገራት እንግዶችና ቱሪስቶች በውድድሩ ላይ ለመታደም እንደሚመጡ የዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኑረዲን ቃሲም ተናግረዋል። የፊታችን ሰኞ ጥር 19 ቀን 2017 ከ 60 ሀገራት 100 ተወዳዳሪዎች እንዲሁም 11 ዳኞች ከሁሉም አህጉር ኢትዮጵያ የሚገቡ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክብር እንግዶች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ዳግም እንደሚገኙ ተገለጿል፡፡ ይህ መድረክ ቱሪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሣብ ቀላል የማይባል ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የቱሪዝም ሚኒስትር፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን…