23
Feb
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው አካባቢዎች ምርጫ እንዲካሄው ውስኗል ተብሏል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ የካቲት 16፣ 2018 ባወጣው መግለጫ ከዚህ በፊት በትግራይ ክልል ስር ሆነው ምርጫ ሲካሄድባቸው የነበሩ ምርጫ ክልሎች ከክልሉ መንግስት ውጪ ሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድባቸው መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሰው ገልጿል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ይካሄድባቸዋል ተብለው በቦርዱ መግለጫ ላይ የተጠቀሱት ምርጫ ክልሎች ሁመራ፣ አዲረመጽ፣ ኮረምኦፍላ ፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች እንደሆኑም ቦርዱ አስታውቋል፡፡ ቦርዱ አክሎም የክልል ምክር ቤት ምርጫ በአካባቢዎቹ ላይ የተነሳባው የይገባኛል ውዝግብ ጥያቄ በህገ መንግስት ውሳኔ መሰረት ሲፈታ እንደሚካሄድ ቦርዱ አስታውቋል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር በበኩሉ…