Business

ኢትዮጵያ ለአምስት ተቋማት የውጭ ምንዛሬ ቢሮ የስራ ፈቃድ ሰጠች

ኢትዮጵያ ለአምስት ተቋማት የውጭ ምንዛሬ ቢሮ የስራ ፈቃድ ሰጠች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት እና ተደራሽነት ለማስፋት ከባንክ ጋር ከተያያዙ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች በተጨማሪ ከባንክ ጋር ዝምድና የሌላቸው የግል የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ መመሪያ አውጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት አምስት የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች መስፈርት በማሟላታቸው የስራ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ባንኩ ገልጿል፡፡ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች መካከል ዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት፣ ግሎባል፣ ሮቡስት እና ዮጋ ፎርኤክስ የተባሉ የግል የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ቢሮዎቹ ሙሉ ተቀባይነት ያላቸው እና የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛት እና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪ እና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሬ…
Read More
ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦት ውድደር ላይ አሸነፉ

ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦት ውድደር ላይ አሸነፉ

195 ሀገራት በተሳተፉበት የሮቦቲክስ ውድድር ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ እድሜያቸዉ ከ14 እስከ 18 የሆኑ 5 ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ከመስከረም 14 እስከ 20 በግሪክ በተከሄደው ዓለም አቀፉ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከ195 በላይ ሀገራት በሚያሳትፈዉ የሮቦቲክስ ዉድድር  ኢትዮጵያን ወክለዉ ችግሮችን እንዴት መፍታት ይችላሉ የሚለው ላይ ትኩረት አድርገው  በውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ በ2024 የፈርስት ግሎባል የሮቦቲክስ ቻሌንጅ  ተማሪዎች  በሮቦቲክስ  በኩል  በሳይንስ፣  በቴክኖሎጂ ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ  መስኮች  ማበረታት  ዓላማ ባደረገው የወደ ፊቱን መመገብ የሚል መርህ ያለው ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ይህ ጭብጥ የሚያተኩረው የአለም የምግብ ዋስትናን እና ዘላቂ የግብርና አሰራሮችን መፍታት ላይ  መሆኑንም ተወዳዳሪዎቹ ተናግረዋል። ኢትዮጲያን የወከሉት ተወዳዳሪዎች ካሌብ ኤርሚያስ፣…
Read More
አቶ አንዷለም አድማሴ ሳፋሪኮምን ተቀላቀሉ

አቶ አንዷለም አድማሴ ሳፋሪኮምን ተቀላቀሉ

የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞው ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አንዷለም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተቀላቅለዋል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንዳስታወቀው የቀድሞውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴን የውጭ ግንኙነት ሃላፊው ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል። አንዷለም የኩባንያው የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ኾነው የተሾሙት፣ የቀድሞው ሃላፊ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ሻወል ከኩባንያው ለቀው ቦይንግ ኩባንያን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ነው። አንዷለም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ያቋቋሙትን አንድ አዲስ የቴሌኮም ኩባንያ በሃላፊነት በመምራት ላይ ነበሩ:: ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የቴሌኮም አገልግሎት ነሀሴ 2014 ዓ.ም ላይ በድሬዳዋ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡ ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለ50 በመቶ ህዝብ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ደግሞ 98 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም አገልግሎት…
Read More
የቻይና ባለሀብቶች ኢትዮጵያን በመልቀቅ ወደ ጎረቤት ሀገራት እየተሰደዱ ነው ተባለ

የቻይና ባለሀብቶች ኢትዮጵያን በመልቀቅ ወደ ጎረቤት ሀገራት እየተሰደዱ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኙት በርካታ የቻይና ባለሃብቶች በሀገሪቱ እያጋጠመን ይገኛል ባሉት ተግዳሮቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት እየሄዱ መሆኑን ገለፁ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ ቀዳሚ የሆኑት የቻይና ባለሀብቶች እና ኩባንያዎች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ ሌሎች ሀገራት እየተሰደዱ መሆኑን ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት የቻይና ባለሃብቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጋጠማቸው በመንግስት አመቺ የስራ ሁኔታዎች እየተሰጠ ባለመሆኑ ወደ ጎሮቤት ሃገራት ማለትም ወደ ኬንያ ፣ ኡጋንዳ እንዲሁም ታንዛኒያ እያማተሩ እንደሚገኙ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተወካይ እንደተናገሩት በብዙ ምክንያቶች ቻይናውያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን ንግዳቸውን ወደ ጎሮቤት አገሮች አዙረዋል ። "ይህ ለኤምባሲው ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ትልቅ ስጋት ነዉ ምክንያቱም የእኛ ተልዕኮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን ትብብር…
Read More
ኢትዮጵያ ግዙፉን የሲሚንቶ ፋብሪካ አስመረቀች

ኢትዮጵያ ግዙፉን የሲሚንቶ ፋብሪካ አስመረቀች

አዲሱ የሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን አንድ መቶ ሃማሳ ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡ ፋብሪካው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡ ፋብሪካው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ልዩ ቦታው ለሚ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የተገነባ ሲሆን ፋብሪካው ከአዲስ አበባ በ134 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። ተገንብቶ ለመጠናቀቅ ሁለት አመታትን ብቻ የወሰደው ፋብሪካ ዘመናዊ የሆነ ከሰው ንክኪ የራቀ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም በመሆኑ የበለጠ ምርት ለማምረት የቀነሰ ኃይል የሚያስፈልገው ነው ተብሏል። በተለይም 174 ሜትር ርዝመት ያለው በአለም ረዥሙ የሆነውን የቅድመ ማሞቂያ ማማ እንደያዘ በምረቃው ወቅት ተገልጿል። የፋብሪካው የማምረት አቅም ከዚህ በፊት በማምረት ላይ ያሉ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን ሃምሳ…
Read More
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ማስተላለፍ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ማስተላለፍ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ኩባንያው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለዘመድ አዝማድ የሚልኩትን ገንዘብ (ሪሚታንስ) በማስተላለፍ አገልግሎት ላይ ለመሠማራት ማቀዱን አስታውቋል። ኩባንያው በዘርፉ መሠማራት የፈለገው፣ የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጡ በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የምንዛሬ ልዩነት ማጥበቡን ተከትሎ ነው ኩባንያው፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሪሚታንስ አስተላላፊነት ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን ከዓለማቀፉ ገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያ ዳሃብሺል ጋር ባለፈው ሐምሌ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከአንድ ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ስራ መጀመሩ አይዘነጋም። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኔትወርክ ማስፋፊያ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድቤያለሁ ብሏል፡፡ ተቋሙ አክሎም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎችበተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ…
Read More
ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዝ ጀመረች ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ዉስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ ያገለገል የነበረዉ የአዳማ - ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁም እንስሳትን ማጓጓዝ ጀምሯል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ እንደገለፁት በአዳማ በኩል የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርትን ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ከመጨመሩም ባሻገር የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል። ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈፃሚው ይህን አገልግሎት በመጀመራችን አቅማችን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል። በባቡር ትራንስፖርት በመጠቀም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው የእንስሳት ንግድ የህገወጥ ንግድ እንቅስቀሴንን ከማስቀረቱ ባለፈ ጊዜ…
Read More
የድቪ 2026 ማመልከቻ ከአንድ ሳምንት በኋላ ይጀመራል

የድቪ 2026 ማመልከቻ ከአንድ ሳምንት በኋላ ይጀመራል

የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1995 ዓመት ጀምሮ በድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ በመውሰድ ለይ ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ ለዚህ እድል ከተፈቀደላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በየዓመቱ በአማካኝ ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ ያቀናሉ፡፡ የድቪ 2024 እድለኛ ኢትዮጵያዊን የቪዛ ማመልከቻቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚያበቃ ሲሆን የድቪ 2025 እድለኞች ደግሞ ከያዝነው መስከረም ወር መጠናቀቅ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የቪዛ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም የድቪ 2026 የማመልከቻ ጊዜ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጀመር ሲሆን ለአንድ ወር እንደሚቆይ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡ የማመልከቻ ጊዜው ከመስከረም 21 ቀን እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 30 ቀናት ይቆያል የተባለ ሲሆን…
Read More
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኛ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኛ ጊዜን አራዘመች

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቦ ነበር የገንዘብ ሚኒስቴር ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ 91.4 ቢሊየን ብር በጀት ይፋ ተደርጓል፡፡ መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ከአንድ ወር በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ የደመወዝ ጭማሪ 2.3 ሚሊየን የፌደራልና የክልል መንግስታት የመንግስት ሰራተኞች፣ 56 ሺህ ተሿሚዎች፣ ለሀገር ደህንነት ሲባል ቁጥራቸው የማይቀመጠው የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የደሞዝ ማሻሻያው ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለዝርዝር የደሞዝ መግለጫው በፃፉት መግቢያ "በተለይም ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ እና ሊደርስ የሚችለውን የኑሮ ጫና በመጠኑም ቢሆን ለመቋቋም እንዲችሉ" የሚል አገላለፅ ተጠቅመዋል፡፡ በጭማሪው…
Read More
ዮሀንስ አያሌው(ዶ/ር) የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ዮሀንስ አያሌው(ዶ/ር) የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጤና እክል ምክንያት ከሃላፊነት የለቀቁት ዮሀንስ አያሌው ብሩ (ዶ/ር)፣ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ  ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሸመዋል፡፡ የአማራ ባንክ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ እንዳጋራው ዩሀንስ አያሌው ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ስራ አስፈጻሚነት መሾማቸውን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ በሰባት ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ከሁለት ዓመት በፊት ስራ የጀመረው የአማራ ባንክ 138 ሺህ ባለ አክስዮኖች የመሰረቱት የግል ባንክም ነው፡፡ ዮሐንስ አያሌው በልማት ባንክ የስራ ዘመናቸው ባንኩ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት  ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ከዚህ ቀደም…
Read More