17
Apr
የትግራይ ታጣቂዎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው ወረዳዎን እና ቀበሌዎችን በሀይል እንደተቆጣጠሩ ተገልጿል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ ህወሓት በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የዘላቂ የሰላም ስምምነት በመጣስ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ፈጽሞብኛል ሲል ከሷል። በፌደራል መንግስት በኩል ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት ለማድረግ መጣሩን የገለጸው ክልሉ፣ ህወሓት የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው በስምምነት አወዛጋቢ ተብለው የተለዩትን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ የኦፍላ፣ የኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን ወርሯል ብሏል። የክልሉ መንግስት እንዳለው ህወሓት ለአራተኛ ዙር ወረራ በመፈጸም በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል ከተካሄዱት "ከባለፉት ሶስት ዙር ደም አፋሳሽ ጦርነቶች" አለመማሩን የሚያሳይ ነው። የአማራ ክልል ወረራ ተፈጽሞባቸዋል ያላቸው ቦታዎች እና የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት በ2013 ጦርነት ከመቀስቀሱ…