04
Jan
ኢትዮጵያ ከአራት ቀናት ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ አዲስ ትኩሳት እንዲፈጠር ምክንያት የሆነ ሲሆን ሀገራት በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ ሱማሊላንድ አንድ አካሌ ናት የምትለው ሶማሊያ ስምምነቱን እንደ ወረራ እንደምትመለከተው ገልጻ ተመድ፣ አፍሪካ ህብረት ፣ የአረብ ሊግ እና ሀገራት ከጎኗ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርባለች፡፡ አሜሪካ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ የሰጠች ሲሆን ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና መስጠት ስህተት እንደሆነ ገልጻለች። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር እንዳሉት "የሶማሊያን ሉዓላዊነት ከማክበር ባለፈ እውቅና ትሰጣለች፣ በአፍሪካ ቀንድ የተፈጠረው አዲስ ውዝግብም ያሳስበናል" ብለዋል። "ሁሉም አካላት ጉዳዩን ከማካረር ሊቆጠቡ ይገባል" ያሉት ቃል አቀባዩ "አለመግባባቱን በዲፕሎማሲያዊ ድርድር ሊፈቱ ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን…